ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 2⃣0⃣ .......ከፊቷ ሄጄ ቆምኩኝ ።… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 2⃣0⃣

.......ከፊቷ ሄጄ ቆምኩኝ ። ልጅቷዐበድንጋጤ ወደዃላ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም !!!
" እ አቤት ምነው ምን አረኩ " አለችኝ በፍራቻ ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ።
የፈራችበት ምክንያት አልገባኝም ነበር ማለት ሰፈር ውስጥ ፀበኛ ተደባዳቢ ነው ስለሚባል ነው ወይስ ለምን ቀና ብላ ለማየት ትፈራኛለች ???
ምክንያቷን ባላውቅ ብቻ ዝም ብዬ ሳያት ነበር ።
ከእኔ አንፃር አጭር የምትባል ልጅ ናት እና እኔን ለማየት የግድ ቀና ማለት አለባት ።
በእጇ የፀሀዩን ግለት ከአይኗ እየጠበቀች
" አቤት ችግር አለ ምን ሆነክ ነው " አለችኝ ። ምን አስቤ እንደሆነ አላውቅም ስታወራኝ ማውራት አቃተኝ !!!
ከእራሴ ጋር የገባውበት ግራ የገባ ስሜት ልረዳው ስላልቻልኩ ከራሴ ጋ መታገል ከብዶኝ ከፊቷ በቆምኩበት ቦታ ቁጢጥ ነገር ብዬ ጭንቅላቴን ይዤ ራሴን ለመረዳት ስሞክር ምንድነው ምን ሆነክ ነው አሞክ ነው እንዴ በአማኑኤል ና ተነስ ....." ብቻ በድንጋጤ ዝምታዋና ፍርሀቷ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ እግሬ ስር ያለሀሳብ ተንበርክክ በስስት አይን እያየችኝ ነበር ስታወራ የነበረው ??በዝምታ እየተመለከቷት ነበረ እና ፊቷን ሳየው ለረጅሞ አመት ተዋውቀን ተግባብተን ተዋደን የቆየን ያህል እየተሰማኝ ነው ???

የሆነ አለ አይደል ብዙ አመት አብሮኝ የቆየ አይነት ሰው በቃ ለእኔ እንደዛ ነው የሚሰማኝ ። ለረጅም ሰአት በሰስት ሳያት ግራ የተጋባችው ልጅ ፊቴን እንደ ጥፊ ነገር ነካ ነካ እያደረገችኝ
" ግን ደህና ነህ ?" አለችኝ ።
አዎ ደህና ነኝ ብዬ ቆምኩኝና አንድ እርምጃ ከሷ ሸሸሁኝ ። እሷም ከተንበረከከችበት ጉልበቷን እየጠረገች ተነሳችና ፊቷን ጨምደድ አድርጋ ለትንሽ ደቂቃዎች ተመለከተችኝና ያንን ወደፊት የመጣ ፀጉሯን ወደዃላ እየወረወረች ጥላኝ ሄደች ።
ስትሄድ ቅሪ አትሂጂ ብላትና አቅፊያት ብቆይ ደስ እንደሚለኝ አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው !!!ግን እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ፊቴንም ሳላዞር ቀጥ ብዬ ወደ እናቴ ቤት ሄድኩኝ ።


የኔ እናት ፊቷ ላይ የሆነ የደበራት ትመስል ነበር ደህና ነሽ እናቴ ? አልኳት አልጋ ላይ እየተጋደምኩ ልጄ እኔ ማንም እንደሌለኝ እያወክ እንዴት እንዲህ ትተወኛለህ ቆይ እ ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እኮ ከኔ ርቀሀል ጠዋት ወተህ ማታ ነው የምትመጣው ምን ነካብኝ ልጄ??  "አለችኝ ሳላስበው ድንጋጤ ውስጤን ወረረው  ምን ያህል እንደተቀየርኩ ብዙ ማሳያዎች አሉ ግን ይሄን ያህል ያስታወቀብኝ አልመሠለኝም ።

ወዲያው ከባድ ንዴት ጭንቀት ፍራቻ የተደበላለቀበት ስሜት ተሰማኝ ።
ከነ ሳሚ ቤተሰብ ጋ በመተዋወቄም ሆነ ሰላምን ጥሩ  ሙድ ላይ ማየቴ ለነሱ ደስታ መፍጠሬ ቢያስደስተኝም ግን በእራሴ እንድናደድ የሚያረግ ሀሳብ በአይምሮዬ እየተመላለሰ አስቸገረኝ !!!
በህይወቴ አንድም ቀን ለእናቴ እንደዛ አይነት ነገር አርጌ አላውቅም ማለቴ ስጦታ ገዝቼላትም አላውቅም !!
ምን አልባትም ያንን ነገር የገዛሁት ለእናቴ ቢሆን ኖሮ ሰፈሩን በእልልታ አድምቃ እየዞረች ልጄ ደረሰልኝ ልጄ የገዛልኝ እያለች እንደምታሳይ እርጥጠኛ ነኝ ማንም ቢሆን ምስክሬ ነው !!!
ለሰላም በማረጌ ባልፀፀትም ለእናቴ ባለማረጌ አበሳጨኝ !!!


ቀኑ እየመሸ ስለነበር ምንም ሌላ እርምጃ ሳልወስድ በዝምታ አዳመጥኳትና ዝም ብዬ ተኛሁ ። ልክ የቀጣዩ እሁድ ቀን በጠዋት ተነስቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ስፖርት ሰርቼ እንጀጨረስኩ ቀጥታ ወደቤት መጣሁኔ እናቴን ጠራዋት ።
ገላዬን ታጥቤ ወጥቼ እስክመጣ ጠጅ ነው የምትይው ቡና ናፍቆኛል እያፈላሽ ጠብቂኝ ብያት ኪሴ ውስጥ ያለችቅንና የደበኳትንም ይዤ ወጣሁኝ ።

ወጥቼ ብሩን ሳይ ሳላስበው ለካ አንድ አንድ እያልኩኝ ጨርሻታለሁ አምስት መቶ ሰባ ብር ናት የቀረች ።
የስፖርት ክፍያ ጌጡን የምገዛበት ሲነሳ አርባ ብር ብቻ እንደሚቀር አሰላሰልኩኝ ።
ገበያ ን አደርገዋለሁ እያልኩ ራሴን እያሳመንኩ ቀጥ ብዬ ስሄድ አሁንም በድጋሜ አየዋት ።
ነፍስ ካወቅን ቡሀላ ምን ተፈጥሮ ሳንተያይ ይሄንን ያህል አመት አስቆጥረን አሁን ቀን በቀን ምክንያቱ ባይገባኝም እንኳን የዛኔ ራሴን ገታ አንርጌ ምንም እንዳልተፈጠረ ቀጥ ብዬ አልፊያት  ሄድኩኝ ። ቀጥታ እዛው ቦታ ላይ ነበረ የሄድኩት ። የሚያማምሩ ጌጣጌጦቼ አሉ ከሰላም በሰጠዋት አይነት ሌላ የሚያምር የአንገጠፈት ጌጥና የእጅ አንባር አየሁኝ ።
እዛ ቆሜ ሳስበው መልስ እንዳለኝ የገመትኩትን ብር አንድ ብርም ሳይመለስ ያኛውም ሳልከፍል ያለችኝን  ሙሉ አጠፋው ። ግን ለእናቴ ስለሆነ ምንም ይሁን ብዬ ሄድኩኝ ። ቤት ስደርስ እንደምፈልጠው የምላ ቀጤማዋን ተጠቅማ ቤቱን የሌለ አሳምራ ጠበቀችኝ ።

እኔም ቸኩዬ እናቴ ነይማ ብዬ ከውጪ ወደ ውስጥ እንድትገባ አረኳትና
ከልጅሽ የሚሰጥሽ ስጦታ አለ ትቀበይኛለሻ አልኳት ፈገግ ብዬ
" ለእኔ ልጅ ?? ምን አስቸገረክ ብር እንዳገኘክ ለራስክ ወይ ልብስም ብትሆን አገዛም ነበር " አለችኝ ።
ከእሳሷ በላይ ለኔ ሟች ናት !!!
ከዛም አሳምራ አስቀምጣ የሰጠችኝና የእጅና የአንገት ጌጥ አውጥቼ ፊት ለፊቷ ያስኩት
በጣም ደንግጣለች ገና እንዳየችው ለእኔ ነው ግን ?? ብላ አነሳችውና ማየት   ስትጀምር በደስታ ተሞልተን እያለ ሰካራሙ አባቴ ከአራት ቀን ቡሀላ በእለተ እሁድ ለዛውም በሰንበት ረፋዱ ገድ ገድ እያለ ወደ ውስጥ ገባ .......
.
.
.
.

ይቀጥላል


#ክፍል_2⃣1⃣
👍4❤2
August 27, 2026 282