ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 1⃣9⃣ ......... ማነው አልኳት ።… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 1⃣9⃣

......... ማነው አልኳት ።
ምክንያቱን ባላቅም በትንሹ ፈገግ አለች ። ለምን እንደሳቀች ባላቅም በእራሴ ፍቅረኛዋን ስላስታወስኳት  በደስታ ነው የምትስቀው ብዬ ደምድሜ ተበሳጭቼ ዝም አልኩኝ ።
" እ እንግዲህ የኔ ፍቅረኛ .......( ረዘም ያለ ዝምታ ) ... ፍቅረኛ ማለቴ ስተት ከሆነ ባላቅም የኔ አማካሪም የምወደውም ወንድሜ ሚስጢረኛዬ ጓደኛዬ ፍቅረኛዬ ሁሉ ነገሬ አባቴ ነው እኔ ያንተን ፍቅረኛ ለማየት ፈልጌ እንጂ ፍቅረኛ የሚባል የለኝም  " ብላኝ አረፈች ።
ሌላጨፍቅረኛ ስለሌላት እና ሁሉ ነገሯ አባቷዐመሆኑ ደስ ቢለኝም መዋሸቷ አያደደኝ ።
ምክንያቱም እኔ በሷ እልህ ማያን ባላስባት እዚህ ግራ የገባው ስሜት ውስጥ ባልገባሁ ነበረ !!!!
ለነገሩ ማን ያቃል ምን አልባት በምክንያት ሊያግባባን ፈልጎ ይሆናል ፈጣሪ ??? ወይስ የቆየ ነገር አሁን ተገልጦልኝ ነው !?? እና ማያን ሳያት ለምንድነው የምደነግጠው ???
.......

በጣም ብዙ ነገሮችን እያሰብኩኝ ከእራሴ ጋር ሀይለኛ የራስ መጋባት ጦርነት ውስጥ ገብቼ አረፍኩት ። ደስ የሚለው ከሀሳቤ ያነቃኝ ከረጅም ሰአታት ቡሀላም ቢሆን ውብ ሆና የመጣችውን ሰላምን ተመለከትኳት ።
በጣም ታሳዝናለች የሆነ የማታውቀው ፍራቻ ሰላም ነስቷታል !!!
በዛ ላይ ቤቱን ልክ እንደ እንግዳ ነው እየዞረች የምትመለከተው !!
ምን ያህል የብቸኝነት ህይወትና የተዘጋ ክፍል እንደከበዳት ፊቷ ማሳያ ይመስለኛል !!! ሳሚም ከዃላዋ መቶ እጇን ይዞ ወንበር ላይ አስቀመጣት ።
የቤት አጋዧ እንዳየቻት  በደስታ አቀፈቻት ስገምት ከድሮ ጀምሮ የቆየች ሰው ናት መሠለኝ !!! ከዛም ቶሎ ምግብ አቀራረበችና መብላት ልንጀምር ስንል በስመአብ ብዬ ቀና ስል ሶስቱም እያለቀሱ ነው ።
ደነገጥኩ  ሳሚ ልዕልና ምንድነው ምን ተፈጠረ አልኳየው ግራ እየተጋባው ።
ልዕልና ከተቀመጠችበት ጠረንጴዛ ብድግ ብላ መጣችና ጥምጥም ብላ አቀፈችኝ ።
በፈጣሪ ስም ሙሉ ሰውነቴ የሆነ ነገር ሲነዝረኝ ተሰማኝ !!!
ወዲያው ለቀቀችኝና እየተቀመጠች
" ማርያምን አንተ ለኛ ባለውለታ ነክ ከላይ የተላክ መልእክተኛ ነክ ብታምንም ባታምንም እንዲ ተቀምጠን ከበላን ከሶስት አመት በላይ ሆኖናል እኮ !!!!!" ብላ መልሳ ማልቀስ ጀመረች ።
ሳሚም ቀበል አድርጎ
" ላንተ ቃል የለኝም  ልጅ ፈጣሪ ይስጥክ " ብሎ ንግግሩን በአጭሩ ገታው ።
ይባስ ብሎ ሰላምም ቀበል አድርጋ 
" ከላይ የተላክ መልአክ ነክ ይሄ ጅማሮ ነው ለእኔ ታስፈልገኛለክ  " ብላኝ አረፈች ።

ሲጀመር ወደዚህ ቤተሰብ የተቀላቀልኩበት መንገድም ግራ የሚያጋባኝ እኔ በዚህ ልክ ሲሄድ በቃ ፈጣሪ በእኔ ላይ አድሮ ስራውን እየሰራ ነው ብዬ አሰብኩ !!!
ግን በምን ስራዬ እንደሆነም አላውቅም !!!! ብቻ ግን በሁኔታዎቹ በጣም ደስተኛ ነኝ!!!በእራሴ እየኮራሁ ነው ሁላ !
ከዛ እንባቸውን ጠራርገው ወደ ምግቡ ተመለስን ። እዛ ቤት ስሄድ የምበላየው ምግቦች በስመአብ እስከ ሁለት ቀን ያቆዩኛል ማለት እችላለሁ !!!

ሀገር አማን ብዬ ምግቡን እያጣጣምኩ እየበላሁ ልጨርስ ስል ያላሰብኩትን ዱብዳ የሆነ ጥያቄ ጠየቁኝ ።
የሳሚ ሚስት ትንሽ እንደበላች ነበር የተነሳችው እናም ቁጭ ብላ ስታፈጥብን ነበር ። ልዕልናም ስትጨርስ
" እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ " አለች ፍልቅልቅ እያለች ። መጀመሪያ ላይ ጉዴን ሳላውቅ የሚያምረው ፈገግታዋን በመመልከት ብቻ አብሪያት ስስቅ ነበር
" ምንድነው ልጄ እሺ ተናገሪ " አላት ።
" እማዬ ከቤት ወታ ስለማታቅ አንድ ቀን ሰብሰብ ብለን የነ  ሚኪ ቤት ሄደን ቤተሰቦቹን እንተዋወቃቸው ደስ አይልም " አለች ምን ደስ የሚል ነገር እንዳወራች ባላውቅም ;መጀመሪያ ሚኪ ስትል እኔን አልመሠለኝም መሠለኝ ዝም ብዬ ነበር
" ደስ አይልም ሚኪ " ስትል ነበር ክው ብዬ አፌ ውስጥ ያለው ምግብ ትን ብሎኝ ልሞት እስክደርስ አስደንብሮን ሁላችንም እስክንጨነቅ ድረስ አሰቃይቶኝ በስንት መከራ ለቀቀኝ !!

በሂወቴ ትልቅ መርዶ ብሰማ ራሱ እንደዛ የምደነግጥ አይመስለኝም በስመአብ !!!
በስንት ስቃይ ከተረጋጋሁ ቡሀላ ሰላምና እሷ ምነው ምንድነው ምን ተፈጠረ ... እያሉ በጥያቄ ቢያስጨንቁኝም ምርጡ ሳሚ ግን ስሜቴን ተረድቶት በዝምታ ተቀምጦ ቆየና በስተመጨረሻም
" ምን ችግር አለ እሁድ ይጋብዘናል ግን እኔ ከቤት ይልቅ መጀመሪያ ካፌ ነገር ብትጋብዘን ባይ ነኝ  " አለና በአይኑ ምልክት ሰጠኝ ።

እ እሺ አረ ችግር የለውም ብቻ ሰላም ይሻላት እንጂ አልኩኝ እየተንተባተብኩኝ ።
ከዛም በቻልኩት ፍጥነትና ምክንያት ደራርቤ ቶሎ ከዛ ቤት ወጣሁ ።
ለእኔ በጣም አስደንጋጭ ጥያቄ ነው ።
ራሴን ካወኩ ጀምሮ በስተት እንኳን የሰው ቤት ገብቼ አላውቅም አድጌ የክላስ ጓደኞቼንም ቢሆን ቤት ላለመውሰድ ነው የነሱ ቤት የማልሄደው !!! የልዕልናን ዘግናኝ ጥያቄ እያሰላሰልኩ ወደቤት ስሄድ  ከፊቴ ማያ ስትመጣ ተመለከትኳት ።
በአጋጣሚ ብዙ ጊዜ እያገኘዋት እንደሆነ ይታወቀኛል !!! ልክ እሷን ሳያት ልዕልናንም ችግሬንም ድንጋጤዬንም ሁሉንም እንድረሳ አድርጋ ትኩረቴን ተቆጣጠረችው!!!
በልቤ ላይ እየተካሄደ ያለው የስሜት  ጨዋታና ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እሷን ማግኘቴ ሲገጣጠምብኝ ላናግራት ወሰንኩ ።
ልክ በአጠገቤ ስታልፍ ምን እንደምላት ሳላስብ እንኳን
ማያ ቁሚ ብዬ ከፊቷ ሄጄ ግትር አልኩ????
.
.
.
.

ይቀጥላል


#ክፍል_2⃣0⃣
❤10
August 26, 2026 333