ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 1⃣8⃣ .........ወደ መታጠቢያ ቤት… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 1⃣8⃣

.........ወደ መታጠቢያ ቤት ሮጥን ።
በር ላይ ስንደርስ እኔ እዛው ቆምኩ ልዕልና በሩን ከፍታ ልትገባ ስትል ከትት ብለው ሲስቁ ሰማን ።
ነገሮች ግራ አጋብተውኝ ልዕልናን ስመለከታት በሩን ኳ ኳ እያደረገች
"  ማ ማ ደህና ነሽ ምንድነው ሰላም ናችሁ " አለቻት። በጭንቀት ልባችን ልትወጣ ደርሳ ነበር ሳሚ ግን ፈገግ ብሎ በሩን ከፍቶ ብቅ አለና ደህና ነን አታስቡ አረ የድሮውን አስታውሰን ነው እኮ " አለ ።

እሱ ላይ ያንን ፈገግታ ማየት ደስ የሚል ነገር ነው ። በባለቤቱ ጉዳይ በጣም እንደተጎዳ ግልፅ ነገር ነው!! በምላሹ ተደስተን ሁለታችንም ተመልሰን ወደ ሳሎን ሄደን ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ተቀመጥን እውነት ለመናገር ረብሾኛል እኔ ከእራሴ ጋ እየተጋጨሁ ነው ደ
እኔ ስለ ፍቅር ምንም የማላውቅ ልጅ አሁን ከራሴም ጋ አልተግባባሁም ።

ሰሞኑን እየተፈጠሩ ባሉት የእንግዳ ስሜቶች ጥርቅም በጣም እየተጎዳሁ ያለሁ ይመስለኛል !!!!
ምክንያቱም ተሰምተውኝ የማላቃቸው ስሜቶች ሁለት በተለያየ አለም በሚኖሩ ሴቶች ላይ እየተሰማኝ ነው ???
የትኛው ስሜት ምን እንደሆነ ራሱ አላውቅም እኔ ስሜቶቹ ምን እንደሆኑ ራሱ አላውቅም !!!
ብቻ  ማያን ሳያት የሚከሰቱት እነዛ የማላቃቸው ስሜቶች አሉ ራሴን አለመቆጣጠር መደንገጥ መወዛገቦች አሉ ???
አሁን ላይ ደግሞ ልዕልናን ሳያት የሆነ ስሜት አለ ደስ ይለኛል እንድትነካኝ አልፈልግም ምክንያቱም የሚፈጠረውን የልብ ንዝረት አልችለውም !!!
ስትቀርበኝ እፈራለሁ !! ሳያት የሆነ የሚያሳሳት ነገር አለ .......እና  ብቻ ግን እኔ ግራ ገብቶኛል እነዚ ቀይ ቆንጆና ጠይም ቆንጆ ሴቶች ግራ አጋቢ ስሜቶችን እያበዙብኝ ነው ያ ደግሞ ለእኔ ጥሩ አይደለም !!!

እኔ ታች ቁጭ ብዬ ልዕልናን ላለማየት አይኔን ሳማትርና ስታገል ነበር ።
ለደቂቃዎች በዝምታ የቆየች ቢሆንም ጭንቀቱ ለቀቅ ሲያደርጋት ነው መሠለኝ
" ደህና ነክ ግን አንተ ?" አለችኝ ጠረንጴዛ ላይ ያስቀመጠውን ኩትን እጅ ነካ እያደረገች ።
እኔ ከአይኗ ለመራቅ ስሞክር እሷ ጭራሽ ያንን ቀይይይይ እና ለስላሳ የሚያንፀባርቅ እጇን ትልክብኛለች ወይ ጉዴ !!!
ደግነቱ ቶሎ እጇን አነሳችለኝ እንጂ ውሀ ሆኜ ነበር !!!ራሴን አረጋግቼ
ደህና ነኝ አረ ምነው ? አልኳት
" እኔንጃ ፊትክ የተረበሽክ ይመስላል " አለችኝ እጆቿን ከአገጯ ጋር እያወዳጀች ።
ስትነካኝ ብደንግጥም እንድትነካኝ ባልፈልገም ሳያት ምናለ እጆቿን አቅፌ በተቀመጥኩ  ከጉንጮቼ ጋር አጣምሬ በቆየሁ ብዬ እመኛለሁኝ !!!


በነገራችን ላይ ስለሁሉም ቁንጅና ተናግሬ ራሴን ዘነጋሁት መሠለኝ ☺️☺️
እና እናቴና ሌሎች በርካታ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ የሚያምር የቆዳ ቀለም ከሚያምር አይን ጋር ሰልካካ አፍንጫ ከተደረደሩና ነጭ ከሆኑ ውብ ጥርሶች ጋር ለስላሳና በመጠኑ ያደገ ፀጉር ስፖርት የጀመርኩት ከብቸኝነት ለመሸሽ እና ጊዜዬን ለማሳለፍ ቢሆንም የሚያምርና የተስተካከለ አቋም ዘመኑን ከዋጀ አለባበስ ጋር ብዙ ነገር ሰቶኛል !!!
ብቻ ምን አደከማቹ ልቅም ያልኩ ቆንጆ ነኝ !!!😂አልፎ አልፎ እነሱን ብጠራጠራቸውም የእናቴ ክብ መስታወት ፊት ስቆም ራሴን እንደ ቆንጆ መቁጠር እጀምራለሁ !!!

ከገባሁበት ራስን የመቆለል ሰመመን ውስጥ ያነቃችኝ " ደግሞ ፍቅረኛክን ሳታስተዋውቀኝ አ " ስትል ነበረ ።

እንደዛ ስትል ማያ ትዝ አለችኝ ግን ከውሸቶቼ መሀል አንድ ልቀንስ ብዬ አስቤ
ያንቺን ባል አስተዋውቂኝ እንጂ እኔ ፍቅረኛ የለኝም አልኳት ።
የሆነ ፈገግታ አየሁባት የምን እንደሆነ አላውቅም ግን ደስ ብሏታል ።
ፍቅረኛ እያላት ምንድነው እንዲ የሚያስደስታት ሆይ ።
ውይ የሀብታም ልጆች ግን ከመቼው ነው ይቺ ልጅ ፍቅረኛ የያዘችው ምናለ ቢያስ ትንሽ ብትቆይ ወይ ቢያንስ ደግሞ ከኔ ጋ ባትተዋወቅ ለነገሩ ከመሠሎቿ ጋ መሆን አለባት ያመኛል እንዴ ........
በጣም ቦዙ ነገሮች እየቀባጠርኩ ብቻዬን ሳወራ ነበረ ። " የኔን ፍቅረኛ እኮ ታቀዋለህ " አለችኝ ። ክው ነው ያልኩት ።
ማ እኔ አልኳት ግራ ገብቶኝ ።
" አዎ ታቀዋለህ እኮ " አለችኝ
ምላሹን የመስማት ፍላጎት ባይኖረኝም
ማነው ?? አልኳት
.
.
.
.

ይቀጥላል


#ክፍል_1⃣9⃣
👍3❤2
August 26, 2026 243