ያልተነገረ ፍቅር ❤️ ❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️ ✍ፊደል ክፍል 1⃣7⃣ .........,እዛው ቁሜ ቀረሁ… — 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 — TG.ME

❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️

❤️ልብ አንጠልጣይ  ታሪክ ❤️

ፊደል

                        ክፍል 1⃣7⃣  

.........,እዛው ቁሜ ቀረሁ ; ከዛ ልዕልናን ዞሬ ሳያት እንዴት እንደተረዳችኝ ባላውቅም ከተቀመጠችበት እየተነሳች
" እማ እሱኮ ሚኪ ነው አስተዋውቅሻለሁ ያልኩሽ ልጅ እሱ ነው ጥሩ ልጅ ነው በዛ ላይ  የአባዬ ጓደኛ ነው እኮ " አለቻት ልክ እኔ በያት ልላት አመት እዳሰብኩት ለዛውም የተሻለ አርጋ አሳመነችልኝ ።
ቀስ ብላ ተረጋጋች አየር እየሳበችና እየተነፈሰች ራሷን አረጋጋች ።
ይቺ ሴት እብድ አይደለችም !!!! ምን ማረግ እንዳለባትም ሆነ ምን እያረገች እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች ራሷን እንዴት እንደምታረጋጋ ሳየቀር ታውቃለች ።
ሰው  ስለበደላት የሰው ጥላቻ ብቻ ነው እሷን የጎዳት  !!!!
እና እሷን ለማረጋጋት በጣም ቀላል ነገር ነው !!!

እኔም እድሌን ተጠቀምኩኝ እግሯ ስር በርከክ ብዬ እያረጋጋዋት
ላንቺ ባይመጥንሽም ስለ አንቺ ስለነገሩኝ ትንሽዬ ስጦታ አምጥቼልሻለሁ ማየት አፈልጊም ?? አልኳት ።
ተመቻችታ እየተቀመጠች ቁጥብ ፈገግታ አሳየችኝ ።ከዛም ብልጭልጭ ቢሆንም በምርጫ ጎበዝ ነኝ መሠለኝ ስጦታውን ሳወጣሁ ሁሉም ተገርመው አዩኝ ሳስበው አልጠበቁም መሠለኝ !!
እሷም በጣም እንደወደደችው እንድገምት የሚያደርግ ፊት አሳየችኝ ።
ከዛም ከማስቀመጫው ላይ አውጥታ እየወሰደች " በጣም ያምራል " አለችኝ በለሆሳስ ።


ድምጿ በጣም ደስ ይላል !!! በዛ ላይ በጣም ቆንጅዬ ናት !!! በርግጠኝነት ሳሚ ራሱን ጥፋተኛ አደረገ እንጂ  በቁንጅናዋና በእድለኝነቷ የተነሳ በቅናት ተገፋፍታ እንዲ ያደረገቻት ይመስለኛል !!!
ግን ምን አይነት ጭካኔ ነው በፈጣሪ የፈለገ ቢሆን እንዴት አብሮ አደግ ጓደኛዋን እንዲ ታደርጋታለች ሴትዮዋን ባቃትና የኔ እናት ብትሆን የምገላት ሁላ መስሎ ተሰማኝ !!!
ብቻ ግን ቃሉ አትፍረድ !! ነውና ፈርጄ ከጨረስኩም ቢሆን አስታውሼ ዝም አልኩኝ ። እኔ ሀብታም ሰዎች አርቴፊሻል ነገር የሚጠቀሙም አይመስለኝም ነበር ፊቴ ላይ ትወረውረው ይሆን እንዴ እያልኩ እየፈራሁ ነበር የሰጠዋት ።
ከጠበኩት በተቃራኒው ግን በጣም እንደወደደችው እየነገረችኝ በፍቅር አይን  እያየችኝ
" አመሠግናለሁ በጣም " አለችኝ ።
ኡፍፍፍ የኔ እናት እርጋታዋ ደርባባነቷ በጣም ነው ደስ የሚለው ።
ረጅምና ለስላሳ ፀጉሯ ሁለት ቦታ እንደተሰራ የቆየ ይመስላል ።
ያ ቀይ ፊቷ በቁስል እና በተቧጨረ ነገር ተሞልቷል ሲመስለኝ ሲያማት ራሷን ለማጥቃት ትሞክራለች መሠለኝ !!!
ግን የተፈጥሮ ውበቷ ያስታውቃል በዛ ላይ ያን ያህል ትልቅ አይደለችም ወጣት የምትባል ሰው ናት !!!


እኔ በሷ ተፈጥሮ እየተመራመርኩ ለካ ሳሚ እያወራ ምን እንዳለ ሳልሰማው " እናመሠግናለን  " ሲል ብቻ ሰማሁት ።
ምን ይበል ምን ባላውቅም አረ አይባል ሳሚ ብዬ ፈገግ አልኩኝ ።
ከዛ እዛ ሀብሉን ልታረገው ስትል
አይ አይ እንደዚ አይደለም መጀመሪያ አንዱን ልዕልና አንዱን ሳሚ ፀጉርሽን ይፈቱታል ከዛ ረጅም ሰአት የሚፈጅ ሻውር ከባለቤትሽ ጋ ትወስጃለሽ ቀስ ብሎ ያጥብሻል ከዛ ልብስ ትቀይሪና ጌጥሽን አድርገሽ ዛሬ ከእኔ ጋር ነው ምሳ የምንበላዎ እንጠብቅሻለን አልኳት መልሷ ምንም ቢሆነን ለመጋፈጥ እየተዘጋጀሁ ።
እንዳሰብኩትም ማልቀስ ጀመረች ስቅስቅ ብላ ካለቀሰች ቡሀላ ወደኔ ተጠግታ ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝና
" የምር እንዳልከው ማረግ እችላለሁ እ ??" ብላ በጥያቄ ፊት አየችኝ ።
እኔም በደስታ ተሞልቼ  አዎ አዎ በደንብ ትችያለሽ በጣም ቀላል ነገር ነው እኮ ትችያለሽ !!!!
ብዬ ለማነቃቃት ሞከርኩኝ ተመቻችታ ተቀምጣ  ዞር ብላ ሳሚን አየችው ።
እሱም እሺ የምትል ስላልመሠለው ችላ ብሎ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም  ስታየው በደስታ ተነስተው ሁለቱም እንደ እንቁላል እየተንከባከቡ በቀስታ ፈቷት ።

በጣም ተጎድቶ ራሱ የሚያምር ፀጉር አላት
ከዛም ወደ ሳሎን ተመልሰን እኔና ልዕልና ቁጭ ብለን ሁሉም ሰላም እንዲሆን እየፀለይን ቆየን ። ከዛም ቀራርቦ  የነበረው ምግብ አንዳንዶቹን እያነሳች ማሞቅ እና ሰላም በፊት ላይ ትወዳቸው የነበሩ ምግቦችና ጁስ መጨመር ጀመረች ።
ልዕልና በጣም ጨንቋት ስትቆም ስትቀመጥ ስትነሳ ስትጨነቅ ነበር እውነት ለመናገር እኔም በጣም ፈርቻለሁ !!!
የሆነ ነገር እንደሚቀየር እያሰብኩ ተጨንቄ ነበር ። እዛው ተቀምጠን ከ አንድ ሰአት ከሀምሳ ደቂቃ በላይ ቆየን !!
አዲስ ነገር ብንጠብቅም ቆዩብን።እስከዛ ሰአት ሰላም መሆናቸው ትንሽ አረጋግቶኝ ልክ ቁጭ ስል የሚረብሽ ጩኸት  ሰማንና ሁለታችንም ለሩጫ እንደተዘጋጀ አትሌት በሩጫ ወደመታጠቢያ ቤት ሮጥን .........
.
.
.
.

ይቀጥላል


#ክፍል_1⃣8⃣
❤11👏4
August 25, 2026 377