❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️
✍ፊደል
ክፍል 1⃣6⃣
........ ከማያ ጋ ተገጣጠምኩ ። በፊት ላይ አግኝቻትም የማላቃት ልጅ አሁን በዚህ ልክ መገጣጠማችን በጣም እያስገረመኝ ነው ።
አሁን አልተሳሳትኩም ራሴን እንደምንም ተቆጣጥሬ አለፍኳት ።
የሆነ አካሌ ግን ያዛት ያዛት ይለኛል ??
ከዛም ምን እንደሚያያዝ ባላውቅም ሀብታም ቤት ሙዝ ይዤ አልሄድም ብዬ ገበያ ውስጥ ስዟዟር የሆነ የሚያምር ጌጣጌጥ ቤት ተመለከትኩኝ ።
አርቴፊሻል ቢሆንም የሚያማምር ሀብልና የእጅ ጌጥ አየሁኝ ።
እና ሚኪ በጣም አስተዋይና አሳቢ ሰው ስለሆነ የሷን መንፈስ የሚያድሱና እሷን የሚያስደስቱ ነገሮች መግዛት ይሻላል ብዬ አሰብኩኝና በሌለኝ ብር መከራከር እንኳን አልችል የሚያምር ሀብልና የእጅ ጌጥ ገዝቼ በእቃ ላይ አስደርጌ ወደነ ሳሚ ቤት ሄድኩኝ ።
ልክ እኔ ስደርስ የሳሚ መኪና ስትገባ ተገጣጠምን ።
ስራ ጨርሶ ምሳ ለመብላት መምጣቱ ነበር ።
እኔም እግር ጥሎኝ እያልኩኝ በአይነት የቀረበው ምግብ ላይ ደረስኩኝ ።
ሚኪ ከባድ የራስ መተማመን ተጭኖታል ።
መኝታ ቤቷን ቆልፋ የምትኖረውን የልዕልናን እናት ሰላምን ጤነኛ ሰው ለማረግ ሀላፊነት ወስዷል ።
ልዕልናም እጇን ተጣጥባ ስትመጣ ከኔ ጋ አይን ለአይን ተገጣጠምን ።
እየሮጠች መታ ጥምጥም ብላ አቀፈችኝ ። ደነገጥኩኝ ክው ብዬ እስክትለቀኝ መጠበቅ ጀመርኩኝ ።
" ትላንት እኮ እናቴን አወራዋት ከስንት ጊዜ ቡሀላ አወራችኝ ስታለቅስ አየዋት በጣም ነው የምናመሠግነው እሺ ደግሞ ስለ አንተ ነግሪያታለሁ እኮ አስተዋውቅሻለሁ ብያታለሁ " ብላ ጉንጬን ሳመችኝ ።
ክው ነው ያልኩት !!! ደንግጬ ፍዝዝ ብዬ ሳያት ምንም ሳትል ዞራ ምግቡ ጋ ቁጭ አለች ።
ወዲያው አንድ የሚገርም ሀሳብ መጣልኝ ቀጥታ ወደ ሳሚ ዞርኩኝና
አንድ ሀሳብ አለኝ !! አልኩ ፈገግ ብዬ
" ምንድነው እሺ " አለኝ ሳሚ ወንበሩ ላይ እየተቀመጠ ።
ወደ ምግብ ከመግባታችን በፊት አንዴ ሰላምን እንያት አልኳቸው ።
ቤቱ በአበቦች ነፈካ ስለሆነ ከማስቀመጫው ላይ አበባ ሳብ ሳብ አርጌ ሁለት አወጣሁ እና ይሄን ይዘን አልኳቸው ።
" አሁን ምሳ ሊቀርብላት ነው ትብላና እናወራለን ከፈለክ " አለኝ ሳሚ በተጨናነቀ ፊት ።
አይ አይ አይሆንም ምግብም አብረን ልንበላ እንችላለን ማን ያውቃል አልኳቸው ።
በጣም ደስ እያለኝ ነው ሀሳቤን የነገርኳቸው !!! ሳስበው ሚኪ ጥሩ የስነ ልቦና ሀኪም መሆን የሚችል ይመስላል !!!
በጣም አስተዋይ ሆኛለሁ ሲጀመር እዚህ ቤት ስመጣ ሌላ የማላቀውን ሰው ነው የምሆነው ። ብቻ ግን መልሳቸውን ስጠብቅ ልዕልና ቀደም ብላ
" ጥሩ ሀሳብ አይመስለኝም " አለች ሳሚም እሷን ተከትሎ
" አዎ አትልፋ አይሆንም እሺ አትልም " አለኝ
ከየት እንዳመጣሁት ባላቅም
ይሆናል !!! ባይሆንም እንሞክረዋ ከሆነ ይሆናል ካልሆነ ቀጣይ ይሆናል ባለፈው ቀን እኮ አምንሀለሁ ብለከኛል እንደምታምነኝ አሳየኛ !!! አልኩት ።
ሳሚም አላሳፈረኝም እሺታውን ለመግለፅ ከተቀመጠበት ተነሳ ።
ልዕልና ሀሳቡን እንዳታስቀይረው ፈርቼ በእጄ ግትቼ ላነሳት ስሞክር ገና እንደያስኳት የሆነ የንዝረት ስሜት ስለተሰማኝ ደንግጬ ቶሎ ለቀኳት ።
ከዛም አበባውን ለሁለቱም ሰጠዋቸውና እናንተ ግቡና እመጣለሁ ብያቸው ወደዃላ ቀረሁ ።
ከዛም ወደ ልዕልና ጠጋ ብዬ
ገብተሽ በደንብ አውሪያትና ከዛ እንግዳ ላስተዋውቅሽ ብለሽ ጥሪኝ አልኳት ቀስ ብዬ እሷም እሺ ብላኝ ወደ ክፍሏ ሄድን ።
ሁለቱም ከመፍራታቸው የተነሳ በሩ ላይ ሲደርሱ ሁለቱም በረጅሙ ተንፍሰው አማትበው ወደ ውስጥ ገቡ ።
ውጪ እያለች ልዕልና በጣም ፈርታ የነበረ ቢሆንም ቀበጥ መሆኗ ጠቀማት መሠለኝ ፍልቅልቅ እያለች
" ማማ አየሽ ምን እንዳመጣንልሽ አበባ ላንቺ ነው እኮ ናፍቀሽን ነበር " አለቻት እቅፏ ውስጥ እየገባች።
ሳሚ ቃላት ማውጣት ስለከበደው በፀጥታ ተውጦ ግንባሯን ሳማትና ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ ።
ከዛም ልዕልና ቶሎ ብላ
" እማ የማስተዋውቅሽ ሰው አለ " ብላ በምልክት ጠራችኝ ።
እስካሁን እነሱን ሲመክርና ሲያበረታታ የነበርኩ ልጅ ለመግባት ራሱ ፈራሁ ከዛ ግን ሳማትብ ለቀቀኝና ፈገግ ብዬ ገና እግሬን ሳስገባ ወደዃላ እየሸሸች መፍራትና መንቀጥቀጥ ጀመረች የሆነ መንፈስ እንዳየ ሰው አረጋት ።
" ከነገርኩህ ጊዜ ጀምሮ ሰው ትፈራለች የማታቀውን ሰው አትወድም ትሸሻለች ነግሬህ ነበር እኮ እንደማይሆን " አለኝ ሳሚ ከተቀመጠበት ተነስቶ በቀስታ ።
የነበረኝ ትልቅ በራስ መተማመን ይጥቀመኝ ይጉዳኝ ባላውቅም በራሴ ተማምኜ
ሊሆን ይችላል ብዬ ወደሷ ቀርቤ ከአልጋው ስር በርከክ ብዬ ስቀመጥ በትልቅ ፍራቻ ታየኝ ጀመር ።
እኔ በሌለኝ ብር አውጥቼ የገዛውት ስጦታ ልሰጣት ከሁዴዬ ውስጥ ፌስታሉን ሳወጣ እሪሪሪ ብላ ጮኸች መረበሽ ጀመረች ትራሶቹን ወረወረችብኝ ማልቀስ ጀመረች .........
በጣም ደነገጥኩ ሳሚ እጄን እየጎተተ እንደወጣ ቢነግረኝም እዛው ቆሜ ቀረሁ .......
.
.
.
.
ይቀጥላል
#ክፍል_1⃣7⃣
6
2August 25, 2026 263