❤️ያልተነገረ ፍቅር ❤️
❤️ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ❤️
✍ፊደል
ክፍል 1⃣4⃣
......... ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ ። እሷም ክው ብሓ እርምጃዋን ገታችው ???
እየተፈጠረ ያለው ነገር ከኔ አልፎ ያስጨነቀው ሳሚ
" ምነው ልጄ ችግር አለ ?" ብሎ እጄን ሲይዘኝ ከገባሁበት ሰመመን ባነን ብዬ
ይቅርታ ሳሚ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ነው !! ብዬ ንግግሬን ገታ አደረኩት ።
እሷም የበለጠ ነጠላውን እየተሸፋፈነች አንገቷን ደፍታ ቄሱን ተከትላ ሄደች ።
ምን እንደተፈጠረና ምን እንደሆንኩ ያልገባኝ እኔ በሀሳብ ተውጬ እያለ ነበር ሳሚ
" ልትነግረኝ ካልፈለክ ተወው በቃ " ያለኝ ።
ለካስ ስለ እራሴ እንድነግረው ሲጠይቀኝ ስለነበር ይሄ ድንጋጤ የተፈጠረው ማውራት ያልፈለኩ መስሎት ነበር ።
እኔም አረ በጭራሽ እንደዛ አይደለምዐበምነግርህ ህይወት ለመገረም ተዘጋጅ እንጂ ነግርሀለሁ አልኩት ።
በመጀመሪያ ትክክለኛ ስሜ ሚኪያስ አይደለም ሀብታሙ ነው ብዬ መናዘዝ ጀመርኩ ። ገና ሳልነግረው የተገረመ ፊት አሳየኝ ። እኔም ፈገግ ብዬ
እኔ የደሀ ልጅ ሆኜ ስሜ ሀብታሙ መሆኑን ስለማልወደው ነው ያስቀየርኩት ።
እና ደግሞ እናቴም አባቴም በጣም ደሀ ከተባለ ቤተሰብ ወተው ደሀ ቤተሰብ መስርተው ይኖራሉ ።
የቤቱ ብቸኛ ልጅ ነኝ ። አባቴ የመጠጥ ሱሰኛ ነው አንድ ካቲካላ ጎንጨት ካላለ የሎብ ምት እንደቆመ ሰው ያረገዋል ።
ሲጠጣ ደግሞ ታርዳ እንደተጣለች ዶሮ ያንፈራግጠዋል !!!
ከልጅነቴ ጀምሮ በድህነት ህይወት ውስጥ ነው ያደኩት ። እናቴ ጉልት ሰርታ ነው ያሳደገችኝ አባቴ አልፎ አልፎ ይሰራል ችግሩ እዛው በካቲካላ ይጨርሳታል ።
እናቴን ያን ያህል ጠባየ ግዛትም እንደገቢያችን ወጪም የለንም እኔ ከጠገብኩ አለም ሁሉ ሰላም ውሎ ያደረ የሚመስላት ምስኪን እናት ናት ያለችኝ ።
" አልጠራጠርም " አለ ሳሚ ጣልቃ ገብቶ ።
በቃ አሁን ላይ የምታነው ሀብታሙን የገነባችው እናቴ ናት ሚኪን ለመገንባት ደግሞ በትንሹ የራሴ ጥረትም አለበት ።
እና አጋጣሚ ከእናንተ ጋር አስተዋወቀኝ እኔ መኖር አለመኖሩንም የማላቀውን አይነት ህይወት ነው የምትኖሩት ።
ደግሞ በፈጣሪ ስም የምምልልክ እኔ በገንዘብ የምገዛ ሰውም አይደለሁም እና ለገንዘብ ብዬ የቀረብኳችሁ ምናምን እንዲመስላችሁ አልፈልግም እኔ በትምህርቴም ደካማ አይደለሁም በጉልበትም ጠንካራ ነኝ በራሴ ሰርቼ ማግኘት የምችል ሰው ነኝ ነገሮች አልመቻች ብለውኝ ነው አልኩት ።
ከሱ ጋ ሳወራ ከልቤ ነው የማወራው እና ለረጅም ደቂቃ በጣም ብዙ ነገር አወራን ከሱ የምደብቅበት ምክንያት የለኝም ለልዕልና ይንገራት አይንገራትም አላሳሰበኝም ሁሉንም ነገር ነገርኩት ።
በጣም ለብዙ ሰአት ነው ያወራነው ደስ የሚለው እሱም በእኔ ላይ ሙሉ እምነት እንዳለው እስከመጨረሻው አብረን እንደምንዘልቅ እኔን እንደ ልጅም እንደ ጓደኛም እንደተቀበለኝ ሙሉ በሙሉ እንደሚያምነኝ ስለ ድህነት ስለ ሀብት እሱም በፊት ላይ ምን አምነት ህይወት እንደነበረው ብቻ በጣም ብዙ ነገር አወራን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በዚህ ልክ የውጪ ሰው ሳወራ ።
ከሰው ብጣላም ከአስተማሪ ብጣላም በድህነት ብከፋም ብቻ ምንም አይነት ነገር ቢኖር እናቴ እቅፍ ውስጥ ገብቼ ነው የማለቅሰው ሌላ የማወራውም የለኝም ።
ከረጅም የግል ንግግር ስንነቃ ነበር ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆናችንም የታወቀኝ ።
ከዛ ተሳልመን ከዛ ወጣን ።
እኔ ተመልሼ ወደነሱ ቤት መሄድ አልፈለኩኝም ። ሳሚ ደግሞ አብረን እንድንሄድ አስቦ ነበር ግን ስራ አለኝ ብዬ ግግም አልኩበት ።
በስተመጨረሻም ቅዳሜ መጥቼ ጠይቃታለሁ ብዬ ቃል ገብቼ እኔም ወደቤቴ በእግሬ መሄድ ጀመርኩ ሳሚም በመኪናው ተመለሰ ።
መንገድ ላይ ሆኜ በርካታ ሀሳቦች ሲመላለሱብኝ ነበር !!!!!
ማያን ሳያት ለምን እንደደነገጥኩ ራሴን ጠየኩት ። አይ ለልዕልና ያወራሁትንና እሷን ስላሰብኩ ስህተት ስለሆነ ነው ብዬ አሰብኩኝና ቀጥ ብዬ መንገዴን ቀጠልኩኝ ። ከሳሚ ጋር ስላወራሁ የሆነ ነገር ቅልል ብሎኛል ።
ስለድህነቴ ለልዕልና ነገራት አልነገራት ብዬ አለመጨነቄ ግን ትንሽ አስጨንቆኛል !!! ዙሪያ ጥምጥም አድርጌ በሩቅ መንገድ አርጌ ብቻዬን እያወራሁ ነበር እየሄድኩ የነበርው ።
የመጨረሻው የኛ ቤት መታጠፊያ ቀጭኗ መንገድ ጋር ስደርስ ግን ከየት መጣች ሳልላት ከፊት ለፊቴ ማያ ስትመጣ አየዋት ።
ሳላስበው ቀጥ ብዬ ቆምኩኝ ።
ለምን እንደሆነ አላቅም ሳያት ሰውነቴ መታዘዝ ያቆም ይመስል የማስበውን ማረግ ከብዶኛል ። ቅድም ለምን እንደቆምኩም ሆነ አሁን መራመድ ለምን እንደከበደኝ አላቅም !!!
ስታየኝ እሷም መደንገጧ ደግሞ የኔን ሀሳብና ጭንቀት አጋጋለብኝ ።
ከሩቅ ስትመጣ ጀምሮ እያየዋት ነበር !!!
ያን ያህል ቆንጆ መሆኗን ያየሁት የዛኔ ነበር ቁመት አቋም ቀሚስ ለባሽ ከእርጋታ ጋር አነውባት ። ቀስ በቀስ ረጠገቤ ደረሰች እሷ አውርቻትም ሆነ ቼክ አድርጊያት ስለማላቅ እንደሁሌው አንገቷን ደፍታ እያለፈች ነበር ። ያቺ ቀጭን መንገድ ግን አቀራርባናለች እና እጄ አልታዘዝ ብሎኝ በሰላም እየሄደች የነበረችውን ልጅ ሳላስበው ቀሚሶቿን ሰብስባ የያዘችበት እጇን ጭምቅ አድርጌ ያስኩት
.
.
.
.
ይቀጥላል
#ክፍል_1⃣5⃣
5
1August 24, 2026 314