ዐማራን ዐማራ የማድረግ ፖለቲካ የዐማራ ብሔርተኝነት ሲባል የሚገነባውም በፖለቲከኛ ዐማራዎች ሳይሆን በብሔርተኛ ዐማራዎች ነው ‼️
የዘር ማጥፋት ድርጊት በዓለም ላይ ከጀመረ ብዙ ምዕተ ዓመታትን እንዳስቆጠረ የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ። የዘር ማጥፋት ድርጊት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ወንጀል ሁኖ ከተመዘገበ ግን ገና አንድ መቶ ዓመት እንኳን አላስቆጠረም። በዓለም አቀፍ መድረክ ዘንድ የዘር ማጥፋት (Genocide) ወንጀል ነው ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ነው። የዘር ማጥፋት ድርጊት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት በላቲን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በአፍሪካ ውስጥ ሲፈጸም ነበር። ይሄ የዘር ማጥፋት ድርጊት ግን በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ወንጀል ተደርጎ አልተሰየመም ነበር።
ምንም እንኮን የአይሁድ ጭፍጨፋ የዓለም የመጀመሪያው የዘርር ጭፍጨፋ ድርጊት ባይሆንም። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜአይሁድን ከመላው አውሮፓ ለማጽዳት የተፈጸመው ድርጅት በዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ "ከባድ ወንጀል" ተብሎ እንዲተረጎም ተደርጓል። በአይሁድ ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት ድርጊት የዘር ማጥፋት "ወንጀል" (Genocide) እንደሆነ በመግለጽ የጻፈው የመጀመሪያው ሰው አይሁዳዊው የፖላንድ ተወላጅ ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን የተባለ ሰው ነው። ይህ ሰው ከናዚዎች ጭፍጨፋ ለማምለጥ ወደ አሜሪካ ሲሄድ በ1944 ሲዊድን ሆኖ "Axis Rule in Occupied Europe" የሚል መጽሐፍ ጽፎ ነበር። በዚህ መጽሐፉ ላይ በአይሁድ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ድርጅት የዘር ማጥፋት ወንጀል አንደሆነ በማያሻማ ቃል ገልጿል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጥቂት የጀርመን ናዚ ባለስልጣናት ተይዘው በኑመምበርግ ውስጥ ለፍርድ ሲቀርቡ ጉዳዩ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲታይ ጠበቃ ለምኪን በየፍርድ ቤቱና በየችሎቱ ሀሳብ መስጠትና መከራከር ጀመረ። ይሁን እንጅ ጉዳዩን ያስቻሉት ዳኞች የናዚ ባለስልጣናትን በጦር ወንጀል ክስ ለመክሰሰ ወሰኑ። ጠበቃ ለምኪን ግን ያለአንዳች ተስፋ መቁረጥ ጫና በማድረግና ደጋግሞ ይግባኝ በማለት በተባበሩት የዓለም መንግስታት ማህበር ጀሮ አንዲሰጠውና በአይሁድ ላይ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ እንዲተረጉምና ውሳኔ እንዲያገኝ፣ በመጪው ዘመንም እንደዚህ አይነት ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ማንቂያ፣ ከተፈጸሙም ወንጀሉ በዚህ እንዲታይ መስፈሮቶችን አርቅቆ የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለምአቀፍ ማህረሰብ ዘንድ በ1948 "ከባድ ወንጀል" ተደርጎ እንዲደነገግ አስቿለ።
የዘር ጭፍጨፋ በዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ "ወንጀል" ተደርጎ ሲደነገግ ፥ ማሟላት ያለባቸው ተብለው የተዘረዘሩ አንቀጾች አሉት። ያም ሁኖ አንድ አንድ ሀገራት ከዚህ ቀደም የፈጸሙት የዘር ጭፍጨፋ ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ወንጀል ሊሆን ስለሚችል አንቀጾች እንዲጠቡ እንደተደረጉ ይነገራል።
የዘር ጭፍጨፋን ወንጀልን የሚጠቁሙና ለዘር ጭፍጨፋ ወንጀል የሚያበቁ ቅድመ ድርጊቶች ውስጥ በሚዲያ፣ በሀገሪቱ ሊቃውንት፣ በመንግስት አካላት የሚደረጉ ስብዕናን የማዋረድ ድርጊት (de-humanization) ትልቁን ስፍራ ይይዛል። የዘር ጭፍጨፋ (Genocide) በአንድ ቀን ጀምበር የሚከናወን ሳይሆን ለረጅም ዓመታት ተደብኖ የሚኖር ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ለዘር ጭፎጨፋ ይመች ዘንድ ልዩ መልክት የተሰጠውን ዘር በቀላሉ እንደ ሰደድ እሳት የሚበላ፣ ሁሉም ቦታ የሚዳረስ ነው። የዘር ጭፍጨፋ ቀስ በቀስ የሚያድግ ድርጊት (heeling-killing process) ነው። የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ የዘር ማጥፋት ድርጊት መሆኑ ሳይነቃ አንድ በአንድ ምልክት የተሰጠውን ዘር እየገደሉ መጨረስ፣ የመንግስት ሚዲያንና አካላትን ተጠቅሞ የሞት ምልክት የተሰጡ የአንድ ዘር አባላት ቀስ በቀስ ቦታውን ለሸው እንዲሰደዱ ማድረግ የዘር ማጥፋት ድርጊት መኖሩን የሚጠቁሙ ናቸው። የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ "ስንች ሰው ሞተ?" የሚል መስፈርት የለም።
ብዙ የዘር ማጥፋት ድርጊት የታየባት ዓለም ሁሉን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ኑራ ፤ በ1948 በይሁዳዊው ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን አማካኝነት እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ከቅድመ እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከ ድህረ ጭፍጨፋ በየፈርጁና በየመስፈርቱ ሰንዷ የዘር ማጥፋት ወንጀልን "ምህረት አልባ ከባድ ወንጀል" በማለት በይና አልፋለች።
ዐማራ ላይ በመልክም፣ በተግባርም፣ በቁጥርም ከቅድመ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፥ ከድህረ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ከተፈጸሙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተከናውኗል። እስከአሁኗ ሰዓት ድረስም እየተፈጸመ ነው። ዐማራ በየሚዲያው፣ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ፣ በየባህላት አዳራሹ ሁሉ ክብሩ፣ ስብዕናው ዝቅ ተደርጎ ተሰድቦ፣ ተዋርዷል። ከአገዳደሉ እስከ አቀባበሩ ድረስ ተዋርዷል። ዐማራ ላይ የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ተደርጎ ካልተቆጠረ ሌሎችማ ምንም ናቸው። ዐማራ በማይጨክንበት የጨከነውም ለዚህ ነው። ዐማራው ላይ የተፈጸመው ወንጀል የሚዳኘው የዓለማቀፋዊ ህግ አግባብ ነው። ፍርድ ቤቱም የተባበሩት የዓለም መንግስታት ፍርድ ቤት ነው። በሀገር ውስጥና በተወሰኑ የፖለቲካ ቡድኖች የሚያልቅ የጓዳ ውስጥ ወንጀል አይደለም። በስልጣን ርክክብም የሚካስ አይደለም። የግድ በወንጀሉ ሃላፊነት የሚወስድ አካል እና የዓለማቀፉ ማህበረሰብም በዐማራ ላይ የተፈጸመው ድርጊት አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን መገንዘብ አለበት። መገንዘብ ብቻም ሳይሆን እያወቁም ይሁን ሳያውቁ ዐማራን ለማጥፋት በሚደረግ ዘመቻ ከመሳሪያ ማቀበል ጀምሮ እስከ ፕሮፓጋንዳ የሰሩ የአውሮፓ፣ የአፍሪካ፣ የየመካከለኛወ ውምስራቅ ሀገራት በድርጊታቸው መጸጸት አለባቸው።
ይሄ የሚሆነው ግን በተባበሩት የዓለም መንግስታት ጫናና ፍላጎት አይደለም። እንደ ጠበቃ ራፋኤል ለምኪን አይነት ባሉ ጀግናና ዓላማ ያላቸው የዐማራ ልጆች ነው።
ዐማራ ላይ የዘር ማጥፋት ድርጊት እንዳይቆም/እንዳያበቃ፣ ወንጀሉም በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይዳኝ የሚያደርጉት የራሳችን ሰዎች ዐማራዎች ናቸው። በተለይም አታጋይ ነን ባይ ግለሰቦች። "ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ" ብለው በዐማራ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በሽምግልና፣ በድርድር፣ በስልጣን ርክክብ ለመጨረስ የሚያልሙ አሉ። እንደ አዎንታዊ ምክንያት ብለው የሚያነሱት ደግሞ "ሰው ለወዳጁ ጫጩት ያርዳል" የሚል የአንድነት ፍቅር ሁነው ለኢትዮጵያ አንድነት ዐማራው ቢታረድም አይቆጨንም የሚል ነው። ዐማራ በተፈጸመበት ልክ ከጸነፈ ወችንም ወንጀሉ ላይ የሚጠብቅ ከሆነ .. ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ላትቀጥል ትችላለች፣ ከዚህ ሁሉ ከባህርዳር ዘንባባ ቆርጠን ፍቅርን ሰብከን "ስለአንድነት፣ ስለአብሮነት እና ስለፍቅር ብለን ሁሉን ተውነው ፤ ከዚህ በኋላ ሰላም ወርዷል" ብለው ታቦት አውጥተው ወይንም ከአባገዳ ዋርካ ስር መታረቅን የመሰለ የለም የሚሉ ናቸወ።
የዐማራ ትገል ወይንም ብሔርተኝነት መሰረታዊ መነሻው፦
1. በማንነቱ ላይ የተፈጸመው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ።
2. ዐማራ ለማጥፋት ዐማራን ሀገር አልባ ለማድረግ የተደረገበት የእርስት ወረራ።
3. የዘር ፍጅቱን ተከላክሎ የዐማራን ትውልድ ማስቀጠልና ዐማራ ዳግም ለዘር ጭፍጨፋ ድርጊት ሰለባ አንዳይሆን ለማድረግ ጠንካራ ዐማራ መፍጠርና የዐማራን የዘር ፍጅት የሚከላከል ዐማራ ወዳድ ስርዓተ መንግሰትና ሀገር መትከል ነው።
1October 19, 2024 332