"3ኛው የዓለም ጦርነት የሚነሳ ይመስልዎታል?" ተብሎ ለተጠየቀ አንድ ጥያቄ አንድ ብልህ የዐማራ ሰው እንዲህ ሲል ይመልሳል "ስለዚህ ጉዳይ ትንቢት መናገር የሚችሉት ኃያላን መንግስታት ብቻ ናቸው።" ወደ ዐማርኛ ሲተረጎም ኃይል ያለው ሁሉም አለው ነወ። ዐማራ ህልውናውን ለማስጠበቅ ኃይል እንደሚያስፈልገው አርሶአደሩም ተረድቶ ልጄን ለፋኖ ብሎ ቃል ገብቶ ልጁን ለዐማራ ወታደራዊ ኃይል ፋኖ በፈቃዱ ራስህንና ወገንህን አስከብር ብሎ ሸልሞ ሰጦታል። በ70 እና በ 80 አመታቸው በወገባቸው ዝናር ታጥቀው የዐማራን ተራሮችና ሸለቆች፣ ቁጥቋጦዎችና ሜዳውች ላይ ሲያገሱ የሚውሉ አዛውንት አንበሶች ይሄን ኃይል ለማዋለድ ሒሳብ በመስራት ነው። ርዕዮት አይጠይቁ፣ መሪ ብቻ ክተት ለህልውናህ ብለዋል። እንደዘመናዊ ሰው ደግሞ ፖለቲከኞች ይሄን ነገር በአግባቡ ተቆጣጥሮ ወደተፈለገው ግብ ማድረስ የሚያስችል በቂ የሆህ መርከብ ማዘጋጀት ይገባቸዋል። ይሄ በሳል ሰው ይቀጥልና ፋኖን ስለማጠያከርና የዐማራ የህልውናም የሉዓላዊነትም ጋሻ አድርጎ ስለማጠናከር እንዲህ ይላል። በዓለም ውስጥ አብዛኛው ህዝብ ሰላም ፈላጊና የጦርነትን ጉዳት የሚሰጋ ነው። እኛ ዐማራዎችም ከሰላማዊ ሰዎች ግንባር ቀደሞች ነን። ነገር ግን ሰላምን የሚሹ ሁሉ እንደሚፈልጉት በሰላም ለመኖር አልቻሉም። እኛም እንዲሁ። ሰላምን ብንፈልገውም ሰላም መህን አልቻልነም። ብዙ ወራሪዎች፣ እብሪተኞች፣ ተንኳሾች፣ የህልውና ጠላቶች አሉ። የዓለምን ታሪክ ገጾች በብዛት የያዘው የጦርነት ታሪክ ሁሉ በወራሪነት፣ በአጥፊመት በተነሱ አጥቂዎችና ሰላምንና ነፃነትን በሚፈልጉ ተከላካዮች መካከል የተደረገ ነው። የእኛም ዕጣ ፋንታ ከዚህ የተቀዳ ነው። እኛ ዐማሮች የሚያንሰንን፣ የሚመሳሰለንንም ሆነ የሚበልጠንን ለመውረር ምኞት ኑሮን አያውቅም። ማንም እንዲደፍረን እንዲያጠቃን ግን ፈጽሞ አንፈቅድም። በዚህ ዘመን የመጣንባቸው አስከፊ የዐማራ መጠቃቶች በኢትዮጵያ ወንድሞች የሆነ በመሆኑ ከነገ ዛሬ ይተዋሉ ብለን ዝም ብለን ተወግተናል። አሁን ግን ክፉኛ ፈትኖናልና ለማስቆም ተነስተናል። ስለዚህ ማንንም ለማጥቃትና ለመውረር ሳይሆን የህልውና ጠላታችንን አጥቅቶ ዐማራን ለማስቀጠል የምንጠቀምበት የዐማራ የመከላከያ ኃይል ፋኖ በሰፊው ማጠናከር ግዴታችን ሁኖብናል። የእኛ ብቻ ሰላምን ፈላጊነት የአካባቢውን ወይንሕ የሀገሪቱን ሰላም ሊፈጥር እንደማይችል ያለፉት 30 +አመታት ከበቂ በላይ ማሳያም ማስረጃም ናቸው። በጎረቤቶቻችን ጦርነት ወይንም ጭቅጭቅ አንገባም። አጥፊዎቻችንን ግን ቀንዳቸውን ሰብረን ከመመለስ የተሻለ መድኀኒት እንደማናገኝላቸው ታሪክ በጥሩው መክሮ አስተምሮናል። ለዚህ ኃይላችንን ከማሰልጠን ፣ ማደራጀት፣ ከማስታጠቅ ለአፍታም ልንታቀብ አይገባም። እኛ ዐማሮች ሰዎችን የማንነካ፣ ነፃነታችንን ግን የማናስነካ ነፃ ህዝብ (ዐምሓራ) ነነ። የማንነት ትርጉሜችን ነፃነት፣ እምቢ ባይነት ነው። የራሳችንን ሰላም እንደምንወደው ሁሉ የሰዎችንም ሰላም እናከብራለን። ከማንም ጋር ጠብ ለማጫር የተጓዝንበት መንገድ ኖሩ አያውቅም። ሲመጡብን ግን ትዕግሥት አያስፈልግም። ከልክ በላይ የሆነ የትዕግሥት መንፈስ ለማይገነዘብ የህልውና ባላጋራ ትዕግሥትን ማስናቅና ፈሪነትን በተዘዋዋሪ መንገድ ማሳየት ነው። ለዛም ነው ከሁን በቃን ያልነው። በዐማራ እግር መቆም አማራጭ የሌለው መድኀኒት ነው ያልነው። ዐማራዎች ሆይ፡ ጠንካራና ዐማራዊ ኃይላችንን አደርጅተን ጠላቶቻችን ከእኛ የሚፈልጉትን ሁሉ ማሳጣት አለብን። ያን ጊዜ ለሰላምና ለፍቅር ይፈልጉናል። ይሄን ማድረግ አለብን። ለዚህ ወጥና የጠራ ዓላማ ላይ የቆመ ዐማራዊ ፋኖ ያስፈልገናል ! ፎቶ፡ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ስልጠና መምሪያ ታያቸው ብርሃኑ
3ኛው የዓለም ጦርነት የሚነሳ ይመስልዎታል?" ተብሎ ለተጠየቀ አንድ ጥያቄ አንድ ብልህ የዐማራ ሰው እንዲህ… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME
February 22, 2025 416