በአምባገነን መንግሥት ሥር የመኖር አንደኛው ክፉ ውጤት መንግሥታዊ ሽብርን እንደ ዕለታዊ ሁነት መቀበል ነው።… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME

በአምባገነን መንግሥት ሥር የመኖር አንደኛው ክፉ ውጤት መንግሥታዊ ሽብርን እንደ ዕለታዊ ሁነት መቀበል ነው። ይህን ክፉ ውጤት መቀበል ለጅምላ ግድያ፣ ለጭፍጨፋ፣ እና ለዕልቂት ያለንን የቁጣ ስሜት ያደንዘዋል። አምባገነኖች ሽብርን ሁልጊዜ የሚከተለን የሕይወት ጥላ ያደርጉታል። ከጥላችን ማምለጥ የተሳነን መሆናችንንም ቀስ በቀስ ያስተምሩናል። የኢትዮጵያ አምባገነን መንግሥት የዐማራ ጭፍጨፋን፣ ሽብርን እና ግድያን አስለምዶናል። በጥይት ተደብድቦ መሞት፣ በጅምላ መጨፍጨፈ፣ እርስት መወረስ፣ ሃብት ንብረት መውደም እንደ ተራ ስታትስቲክስ እንድንቆጥር አድርጎናል። ነገር ግን አንዳንዴ ይህን ባስለመዱ አምባገነን ሥርዓቶች ውስጥ እንኳን ሳይቀር በደረጃው ከሁሉ የላቀ፣ በዓይነቱ ከሌሎች መንግሥዊ ሽብሮች ሁሉ ተነጥሎ የሚታይ፣ የህዝብን አዕምሮ እና ልብ ሰቅዞ እና ቀስፎ የሚይዝ ታላቅ መንግስታዊ ሽብር ፥ ታላቅ ፍጅት የዘር ፍጅት ይፈጸማል። በአፓርታይድ የግፍ ሥርዓት ውስጥ በኖሩ ደቡብ አፍሪካውያን ላይ የተካሄደውን የስዌቶ ፍጅት (እ.ኤ.አ 1976) ፣ በአምባገነን ወታደራዊ አመራር ሽብሮችን ቁም ስቅላቸውን ሲያዩ የኖሩ ግብጻውያን የተፈጸመባቸውን የራባን ጭፍጨፋ (እ.ኤ.አ 2013) ፣ በብሪታንያ የኮሎኒያል አገዛዝ ግፍ እና በደል የተሰቃዩ ሕንዶች የወደቀባቸውን የአምሪትሳር ግድያ (እ.ኤ.አ 1919)፣ እና በፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የማያባራ ጥቃት ሲፈጸመባቸው የኖሩ አልጄርያውያን ላይ የወረደባቸው የፊሊፕቪል ዕልቂት (እ.ኤ.አ 1955) በተጠቀሱት አገሮች ዜጎች ከሌሎች መንግሥታዊ ሽብሮች ተለይተው የሚታዩ ናቸው። ፍጅቶቹ፣ ጭፍጨፋዎቹ፣ ግድያዎቹ፣ እና ዕልቂቶቹ ለእነዚህ ሕዝቦች ልዩ ትርጓሜ እና ሥፍራ ያላቸው የታሪክ ምዕራፎቻቸው ናቸው። በዐማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋም ከእነዚህ ታሪካዊ መንግስታዊ ሽብሮች ተርታ የሚመደብ ባይሆንም እንኳን የመንግስታዊ ሽብርን እስከ ዘር ማጥፋት ያለውን ደረጃ አጉልቶ ያሳየናል። መንግስታዊ ሽብር የአንድን ህዝብ ህልውና የሚገዳደር አደገኛ ሂደት ነው።አንድን ህዝብ ጦር ሰብቆ ለማጥፋት ይከብድ ይሆናል። መንግስታዊ መንበሩን ይዞ፤ በስመ መንግስት ነኝ የሚደረግ ማንነት ተኮር መንግስታዊ ሽብር ግን ለህልውና አደገኛ ነው። አውሮፓውያን በአይሁዳውያን ላይ ስም ለጥፈው በህብረት ተነስተቅ ለማኝፋት ጦር ሰብቀው ነበር። ያ ዕቅድ በተባበረ የአይሁዳውያን ክንድ መክሸፍ ችላል። የመካከለኛው ምስራቅ የታላቁ የባዛንታይን ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ ታላቁ የኩርድ ህዝብ የጠፋበት እና ሀገር አልባ የሆነበት መንገድ ፤ ኩርዲስታን ላይ የወደቀው አደጋ ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ መንግስት መር ነበር። ይጠብቀናል በሚሉት፣ መብታችንን ያስከብራል፣ ሀገራችንን ያቀናል ብለው በሚያስቡት፣ ግብር በሚከፍሉት መንግስት ጸረ ኩርድ ንቅናቄ ከውስጥ ፈንቅሎ ወጣ። ያንን ከነገ ዛሬ ይቀራል ሲሉ ጠቅልሎ እንደበላቸው አይተናል። የዐማራን የህልውና አደጋ ክፉ የሚያደርገው ጠላቱ ውስጣዊ መሆኑ ነው። "ቅድስት ሀገሬን ይመራል፣ ሉዓላዊነቴን ያስከብራል" ብሎ በሚያምነው በራሱ መንግስት ጸረ ዐማራ ሽብር እስከ ፈጽሞ ማጥፋት ዕቅድ ወጥቶለት በቅደም ተከተል ጭፍጨፋ እየተፈጸመበት ያለ ነው። ይህ ዘመን ለዐማራው ታሪካዊ ዘመን ነው። ይህ ዘመን ነገ የዐማራ ትውልድ በዛ ዘመን እያለ የሚያወሳው ለታሪክ የሚቀመጥ ነው። የሚያሳዝነው ለሰላሳ አመታት የቀጠሉት የዐማራ ግዙፍ ጭፍጨፋዎች አንዱም አልተመዘገቡም። ጭፍጨፋው ዕቅና አላገኘም። በራሱ በዐማራም በውጭ አካላትም። በአንድ ወቅት እ.ኤ.አ በ2014 የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች በግብጽ ራባ አደባባይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ “ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በአንድ ቀን ከተፈጸሙ ታላላቅ ግድያዎች መካከል አንዱ” ተብሎ እንደሚመደብ ዘግቧል ነበር። እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከዚህ የራባ ግድያ ጋራ የሚወዳደሩት የቻይና ታይናሚን እና የኡዝቤኪስታን አንዲጃን ጭፍጨፋዎች ናቸው በማለት አስፍሮ ነበር። በእነዚህ ሁሉ ታላላቅ ጭፍጨፋዎች በእያንዳንዳቸው የሞተው ሰው ቁጥር ከአራት መቶ እስከ ስምንት መቶ የሚገመት ነው። የዓለም ሚዲያና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ታላላቅ ጭፍጨፋዎች ሲል መዝግቦ አልፏቸዋል። ዐማራ ላይ የተደረገው ግልፅ እና መንግስታዊ የዘር ፍጅት ከእነዚህ ቁጥሮች ጋር ሲወዳደር የአንድ ቀኑ ይበልጣል። የስዊድኑ ኡፕሳላ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ ከ1946 ጀምሮ በዓለም የተፈጸሙ የተደራጁ ሽብሮችን የሚመለከት ገላጭ መረጃዎችን ያቀፈ፣ ድንቅ ዳታ ቤዝ አለው። የዊኪ ፕሮጀክት ደግሞ የዓለም ጭፍጨፋዎችን (massacres) የሚያጠናክር በየጊዜው የሚያዘምን (dynamic) የመረጃ ዴፖ አለው። የትጥቅ ግጭትን፣ ከአንድ ቀን በላይ የወሰዱ ጭፍጨፋዎችን እና ከመንግሥት ውጪ የተፈጸሙ ፍጅቶችን ወደ ጎን አድርገን ሁለቱንም ዳታ ቤዞች ስንመረምር ዐማራ ላይ የተፈጸመውን ያክል በዓለም ላይ የትኛውም ሀገር የትኛውም ህዝብ ላይ እንዳልተፈጸመ እናረጋግጣለን። ግን አየሁ ሰማሁ ባይ የለም። ቢፓን ቻንድራ “Indian’s Struggle for Independence” በተሰኘው ታዋቂ መጽሐፋቸው የአምሪትሳርን ጭፍጨፋ በተመለከተ ሲያትቱ የሕንድን ሕዝብ ክፉኛ ድንጋጤ እና ከፍተኛ ቁጣ ውስጥ የከተተው የሟቾች ቁጥር ሳይኾን ግድያው የተፈጸመበት መድረክ መኾኑን ያወሳሉ። በዚህ ጭፍጨፋ የተገደሉት በፑንጃብ ግዛት በየዓመቱ በደማቅ ሁኔታ በሚከበረው የመኸር የእህል ምርት የምስጋና በዐል (Harvest Thanksgiving) ላይ ለመታደም የተሰበሰቡ ሰዎች ናቸው። ቻንድራ እንደሚሉት ከዚያ ጭፍጨፋ በኋላ በሕንዶች እና በብርታኒያዊ ገዢዎቻቸው መካከል ያለው ግንኙነት ፈጽሞ ተቀየረ። ሕንዶች በአገዛዙ ላይ ያለቸው ተስፋ ተሟጦ አለቀ። ታላቁ የሕንድ ጸረ ኮሎኒያሊዝም ትግል ተቀጣጠለ። አምሪትሳር በሕንድ እና በብሪታንያ የታሪክ ትምህርት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ነው። የዐማራን ህዝብ ወደ ቁጣና በመንግስታዊ ሽብር ቡድኑ ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ ሁነቶች ብዙ ነበሩ። ጅምላ መቃብሮች፣ የዘር ፍጅቶች አላስደነገጡንም። አላስቆጡንም። የድል በዓሉን አድዋን አታከብርም መባሉም አላስቆጣም። ከክልሉ ውጭና ውስጥ ለሽብር ሰለባ መሆኑም አልገረመንም። ወደ አዲስአበባ እንዳትገባ መባሉም አልመሰለንም። የዚህ ሁሉ ጣጣ መውጫ መንገድ አንድ ነው። የዐማራ ህዝብ አይኑን የሸፈነበትን "የኢትዮጵያ" መሀረብ ማውለቅ ነው። ያኔ እየተደረገበት ያለው መከራ ሳይሆን መውጫ መንገዱ እንደ በጋ ሰማይ ጠርቶ ይታየዋል!! 9 ሚሊዮን ህዝብ የተጨፈጨፈበት አንድም ሀገር አንድም ህዝብ የለም። እኛ ብቻ !!

March 25, 2025 590