የህልውና ትግል ውስጥ ያለ እውነተኛ መሪ፤ መሪ ብቻ ሳይሆን የትግሉም ህያው መገለጫ ነው። የህዝባችንን የተስፋ ክብደት መሸከም፣ ከፍተኛ ጫናን መቋቋም እና የትግሉን እንቅስቃሴ በውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ስጋት ውስጥ እንዳይወድቅ ማረጋገጥ ያለበት ነው። አንድ መኪና ወይንም ጀልባ ፣ አውሮፕላን ወይንም ባቡር ያለመሪ ሊቆም እንደማይችለው ሁሉ ፤ ህዝብ ያለመሪ አይነ ስውር ነው። ለዛም ነው ላለፉት 50+ አመታት ዐማራ ያለመሪ በመሆኑ ገደል ሲገባ፣ ገደል ሲጣል የኖረው ‼️ እኛ ዐማራዎች ለመሪዎቻችን ያለንን አክብሮታ ለመግለጽ ይመስላል አባቶቻችን "ስዩመ እግዚአብሔር" ብለው የሚጠሩት። ጥሩን ብለው ሳይሆን በህዝብ፣ በጳጳሳት ተሹመው ! ይሄ ሲሆን ሲያጠፋ "ስዩመ እግዚአብሔር" ስለሆነ በመሪ ላይ ማመጽ በእግዚአብሔር ላይ እንደ ማመጽ ነው አይባልም። አክብረን የማይከበረውን ነጥለን እየጣልን ዐማራን ማዳን ነው ስራችን። ምክንያቱ "ከስዩመ እግዚአብሔር" መሪ ይልቅ "ስዩመ እግዚአብሔር" ህዝብ ይበልጣል። በዚህ ምስሌ የእኛ መሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው 👇👇 የፋኖ መሪዎች የፋኖን ትግል ለመምራት ከዚህ በኋላ ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎች ላይ መጠየቅ አለባቸው። ሀ/ ግልጽ ርዕዮተ ዓለም እና ግብ በተመለከተ የዐማራ ፋኖ መሪዎች መጠየቅ አለባቸው። "የዐማራ ህልው" የሚለው መነሻ ምክንያት እንደ ግብምና ርዕዮተዓለም ሁኖ ሊያገለግል አይችልም። አንድ የፋኖ ከፍተኛ መሪ ስለርዕዮተዓለም ሲያስረዳ "የዐማራ የህልውና ጥያቄ ነው ግባችን" ሲል ሰማሁት። ይሄ ስህተት ነው። ዛሬ ላይ ታጋዮችና የትግል ደጋፊዎች ምን ለመሆን፣ ምን ለማሳካት፣ የት ለመድረስ ነው የምንታገለው ሲሉ ጥያቄያቸው መልስ ማግኘት አለበት። ይሄን ለጠየቀ የትግል ደጋፊና ታጋይ "ለህልውናህ ነው የምትታገል" ማለት አጥጋቢ መልስ አይደለም። ምክንያቱ ደግሞ ለዐማራ ህልውና ነው የምንታገል እያሉ ፤ ለዐማራ ህልውና ግን አደጋ የሆኑ ሰዎችና ቡድኖች በርካታ ስለሆኑ። እርስ በእርስ መከባበር ሲጠፋ፣ በየቀበሌና በየሸጡ መፎካከር ሲመጣ፣ የመሪው አቅም እየደከመ ሲመጣ፣ መሪዎች እንኳንስ የዐማራን የሀይማኖት፣ የኢትዮጵያዊነት፣ የሰፈር .... ሌሎችን ኮንፊውዥን ሊፈቱና በነገዱ ዐማራን አንድ አድርገው ሊያታግሉ ቀርቶ እርስ በእርስ በእጅ አዙር ወደ መዘላለፍና የሰፈርና የቀበሌ ሊቀመንበር አይነት ባህሪ ሲያዳብሩ ... ታጋዩና ደጋፊው መጨረሻው የት ነው ብሎ ወደ ኋላ ማፈግፈጉ አልቀረም። ከዐማራ የእኛ ጎጥ የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ ከማለት ፤ ከእኛ ጎጥ ደግሞ የእኛ ቀበሌ በልዩ ሁኔታ የአንበሳውን ድርሻ ይውሰድ ማለት ላይ ደርረናል። ይሄ ከርዕዮተዓለም እና ግብ አልባነት የመነጨ ድርጅታዊ ህመም ነው። ሲጠቃለል መሪው የትግሉን የመጨረሻ ዓላማ መግለፅ እና ሁሉም አባላት እንዲረዱት እና እንዲያምኑበት ማረጋገጥ አለበት። ለ/ የአባላትን ዲሲፕሊን ጥሰት፣ የውስጥ አንድነት ክፍተትን ለመከላከል ጠንካራ የትዕዛዝ መዋቅር መመስረት ያስፈልጋል። ሶስት መስመር ጹሁፍ እየጻፉ የሚያንገራግሩ የሻለቃና የብርጌድ አመራሮች የበዙበት ጠንካራ የትዕዛዝ መዋቅር ባለመኖሩ ነው። ማን አለብኝነት ከድርጅቱ በላይ ገኖ ወጥቷል። የአመራር ሚናዎች፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች እና የአተገባበር ሰንሰለቶች በሚገባ የተገለጹ መሆን አለባቸው። ጥብቅ የስነምግባር ህግን ማዳበር፣ አባላት ተግሣጽን መከተል አለባቸው። ክህደትን ማስወገድ፣ አንጃ ፈጣሪነትንና ለዐማራ የውስጥ አንድነት የጭቃ ውስጥ እሾህነትን አጥብቆ ማስቆም፣ ቀይ መስመር ማድረግ ያስፈልጋል። አጠቃላይ የትግል የእንቅስቃሴዎችን፣ መርሆችን ያለምንም ልዩነት ማስከበር ያስፈልጋል። ይሄ ካልሆነ የተበተነ ኃይል ለዐማራ ነቀርሳ ነው። ይሄ አባላቱን ሳይሆን መሪውችን የነገ ታሪክ የሚያጠም፣ ለዐማራም የመከራ ዶፍ ማጋትም ነው። ሐ/ ከተቻለ በአባላቱ አልሆን ሲል ደግሞ ከላይ እስከ ታች በድርጅታዊ መዋቅሩ መሰረት የጋራ ሃላፊነትን ማበረታታት ወሳኝነት አለው። ስራ አስፈጻሚው እንኳን መተማመን፣ መከባበር፣ መዋደድና አንድ መሆን አለበት። እያንዳንዱ አባል በትግሉ ላይ የባለቤትነት ስሜት ሊሰማው ይገባል። ይህም ለስኬታማነቱ የበለጠ ቁርጠኛ ያደርገዋል። ያ ማለት ግልጽ በሆነ check and balance ከአባላቱ ጀምሮ እስከ አመራሩ ድረስ የራሱ ድርሻና ሚና ቢሰጠው ጠንካራ ይሆናል። መ/ የአንድ የፖለቲካ ትግል የጀርባ አጥንት የሚሆነው መደበኛ ስልጠና እና የፖለቲካ ትምህርት ማዳረስ ነው። ለሁሉም ማህበረሰብ ካልሆነ ግን በትግሉ ማዕቀፍ ውስጥ ላሉ አባላቱ የፖለቲካ ትምህርትና ስልጠና መስጠን ወደር አልባ ጥቅም ያለው ነው። ሁለቱም የርዕዮተ ዓለም እና ተግባራዊ ወታደራዊ/ፖለቲካዊ ስልጠና አባላት የተካኑ እና የተማሩ እንዲሆኑ ማድረግ ከዛም ባሻገር ማረጋገጥ ያስፈልጋል። Mass doesn't matter! በማዕበል አትመኩ። ማዕበል የሚያገለግለው ሰላማዊ ተቃውሞ ላይ ነው። በትጥቅ ትግል ላይ የሰለጠኑና ለዓላማቸው ሊሞቱ የተዘጋጁ ጥቂት የተደራጁ ኃይሎች በቂ ናቸው። ሒደቱ ሲጨምር ብዙሀኑ ያስፈልጋል። ለእኛ ደግሞ ዕድል ነው። ዐማራ በህብረት ነው የተነሳው። ስራው ከብዙው መምረጡ እና ያንን ዐማራ አድርጎ ማስታጠቁ ነው። ሠ/ የፋኖ መሪዎች ዋና ትኩረት አድርገው መስራት ያለባቸው የውስጥ ግጭቶችን መከላከል ከተቻለ ማስቀረት ነው። ማስቀረት ባይቻል ሲከሰቱ ትክክለኛ መፍትሄ እየሰጡ፣ እየተከላከሉ የውስጥ አንድነትን፣ የአባላቱ መተማመንን፣ መከባበርንና ፍቅርን መገንባት ነው። መሪ የውስጥና የአባላት አለመግባባቶችን በፍጥነት እና በትክክል መፍታት አለበት። ውስጣዊ ክፍፍል አጠቃላይ የትግል እንቅስቃሴውን እንዳያዳክም፣ ተምሳሌታዊነት ትምህርት እየሰጡ እና ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬን እየገነቡ መከላከል አለባቸው። የትግሉ ደጋፊና ታጋይ የዐማራን የህልውና ስጋት መሰረት፣ የዐማራን ህዝብ ነገዳዊ ታሪክ ማገርና የጉልላቱ ማነጫ አድርገው ድርጅቱን ማቆም፣ መጠገን፣ ማጎልበት አለባቸው። ጠንካራ መሪ ጠንካራ ህዝብ ይወልዳል !
የህልውና ትግል ውስጥ ያለ እውነተኛ መሪ፤ መሪ ብቻ ሳይሆን የትግሉም ህያው መገለጫ ነው። የህዝባችንን የተስፋ… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME
March 16, 2025 548