ዐማራው ሞት ለዐማራ ብሔርተኝነት ፤ ድል ኢትዮጵያ አንድነት ቢልም የሞት ዘመን ቢያስረዝም እንጅ የሚያገኘው… — State of Amhara (ነጣ የዐማራ መንግስት) — TG.ME

ዐማራው ሞት ለዐማራ ብሔርተኝነት ፤ ድል ኢትዮጵያ አንድነት ቢልም የሞት ዘመን ቢያስረዝም እንጅ የሚያገኘው ፖለቲካዊም ሆነ ፤ ዐማራዊ ትርፍ የለውም ‼️

በጸረ ሴማዊ እንቅስቃሴ ወቅት በአውሮፓ የሚኖር ይሁዲ ሁሉ የግድያ ምልክት ተሰጥቶት ነበር። ያ የግድያ ምልክት ድሬይፉስ የሚባል የሚባልሰው ላይ ደረሰ። ድሬይፉስ በፈረንሳይ የሚኖር ይሁዲ ነበር አሉ። ይሁዲነቱ ለጥቃት አጋለጠው። ያለ ጥፋቱ “ከውጭ ከጀርመን ጋራ ተመሳጥረሃል” ተባለ። "ከጀርመን ጋር ተመሳጥረሃል" ያሉት በይሁዲነቱ ሊገድሉት ምክንያት ሲፈጥሩለት ነው። ከቀናትም በኋላ የነበረዎ ማዕርግ ተገፈፈ፣ በአደባባይ ተዋረደ፣ ተገረፈ። ድሬይፉስ ግን “ንጹህ ነኝ፥ ንጹህ ነኝ የማውቀው ነገር የለም ብሎ ማለ። ያምኑት ዘንድም "ድል ለፈረንሳይ” እያለ እጁን ዘረጋ። ግን ምን ያደርጋል ይሁዲ ነው። ምንም ቢል ከጸረ ሴማዊ አሳዳጆች አይተርፍም። በከንቱ ጉንጩን አለፋ ! እውነቱን የሚሰማው አልነበረም።

በጸረ ሴማዊ እንቅስቃሴ ወቅት በአውሮፓ የሚኖር ይሁዲ ሁሉ የግድያ ምልክት ተሰጥቶት ነበር። ያ የግድያ ምልክት ድሬይፉስ የሚባል የሚባልሰው ላይ ደረሰ። ድሬይፉስ በፈረንሳይ የሚኖር ይሁዲ ነበር አሉ። ይሁዲነቱ ለጥቃት አጋለጠው። ያለ ጥፋቱ “ከውጭ ከጀርመን ጋራ ተመሳጥረሃል” ተባለ። "ከጀርመን ጋር ተመሳጥረሃል" ያሉት በይሁዲነቱ ሊገድሉት ምክንያት ሲፈጥሩለት ነው። ከቀናትም በኋላ የነበረዎ ማዕርግ ተገፈፈ፣ በአደባባይ ተዋረደ፣ ተገረፈ። ድሬይፉስ ግን “ንጹህ ነኝ፥ ንጹህ ነኝ የማውቀው ነገር የለም ብሎ ማለ። ያምኑት ዘንድም "ድል ለፈረንሳይ” እያለ እጁን ዘረጋ። ግን ምን ያደርጋል ይሁዲ ነው። እውነቱን የሚሰማው/የሚቀበለው አልነበረም።

ድሬይፉስ ይሄን ሁሉ ማንነታዊ ጥቃት ሲያስተናግድ፣ ማንነቱን ክዶም "ድል ለፈረንሳይ" ቢል ከጸረ ሴማዊ አዳኞች መትረፍ ከልቻለም። ይህን ጊዜ አንድ ጋዜጠኛ ግን ሁነቱን ይከታተል ነበር። ጋዜጠኛው ቴዎዶር ሄርጽል ነው። ይህ ይሁዲ ሲዘለፍ፥ ሲሰደብና ሲዳፋ ይህ ጋዜጠኛ ይሁዲ ሁነቱን ይከታተል/ ይመለከት ነበር። ከሁሉም በላይ ከተሰነዘሩ ስድቦች መካከል “ሞት ለአይሁድ” የሚለው ከጋዜጠኛው ከቴዎዶር ሄርጽል አእምሮ ውስጥ ሳይወጣ አቃጨለበት። "ሞት ለአይሁድ" የሚለውን ድምጽ ከሰማ በኋላ ሄርጽል እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም። ይበልጥ ግን ለአይሁድ ሀገር ምሥረታ ተጋ። ተሳዳቢዎች ባይኖሩ፥ የድሬይፉስ መዋረድ ባይኖር ይህ ታላቅ ጽዮናዊ ስለ አይሁድ ሀገር ባላሰበና በተዘናጋ ነበር። ከድሬይፉስ ፍርድ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሄርጽል በባስል የመጀመሪያውን የጽዮናውያን ሸንጎ ስለ ማካሄዱ እንዲህ ሲል ማስታወሻውን ከተበ። “በባስል የአይሁድን ሀገር መሠረትኩ። ዛሬ ይህን በጉልህ ብናገር፥ በሁሉም ዘንድ በሳቅ ይመለስልኝ ይሆናል። ምናልባት በአምስት ዓመት ውስጥ፥ በርግጥም በሀምሳ፥ ሁሉም ይህን የዛሬ ንግግሬን ይረዳል። ለአይሁድ ሀገር ምስረታ በጽናት መነሳት አለብን ይሄን ካላደረግን በህይወት ለዘር አንተርፍም” ሲል ንግግሩን ቋጨ።

ቴዎዶር ሄርጽል ይሄን ጉባኤው 1897 አደረገ። እሥራኤል ደግሞ በ1948 ዓ.እ ተመሠረተች። ከሀምሳ አንድ ዓመት በኋላ ማለት ነው። ይህ ሰው ትንቢተኛ ነው ይሉታል። በቤተ መንግሥቱ ግድግዳ የዚህ ትምቢተኛ ፎቶና ስም ተሰቅሏል፣ ከሀገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ከፍ ተደርጎ ይዘመራል። ያ ቀልድ የሚመስለው የቴዎዶር ሄርጽል ንግግር ይሄው እውን ሆነ።

ዐማራ በዐማራ ፖለቲካ ላይ የማይጸና ከሆነና በራሱ የፖለቲካ እግር ካልቆመ "የዐማራ ብሔርተኛ" ነኝ የሚለውን ቀልድ ፤ ቀልዱም በዐማራ ህዝብ ላይ መቀለድ ነው !
❤1
October 17, 2024 378