#ጤናመረጃ
ለፈጣን የፀጉር እድገት የሚረዱ ተፈጥሯዊ ዘዴዎች!
1- ሩዝ መጠቀም
2 የቡና ስኒ ሩዝ በ2 ኩባያ ዉኃ ለ5 ደቂቃ ያህል ማፍላት፣ዉኃዉን አጥልለን ለብ ሲል ፀጉራችንን አዳርሰን በመቀባት ለጥቂት ደቂቃዎች ቆዳችንን ማሳጅ ማድረግ፣ ከ30-45 ደቂቃ ያህል አቆይተን መታጠብ ለፀጉር እድገትና ልስላሴ ተመራጭ ነዉ፡፡
2- ቀይ ሽንኩርት
ሽንኩርት ዉኃ ዉስጥ በመቀቀል በዉኃዉ ፀጉሮን መታጠብ እና አቆይቶ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ፣ ከዛም ውጤቱን መመልከት፡፡
3- የኮኮናት ዘይት
በየቀኑ የኮኮናት ዘይት በማሞቅ የፀጉርን ቆዳ አዳርሶ በመቀባት የፀጉርን ቆዳ ለ1 ደቂቃ በማሸት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ዉጤቱን ማየት ይችላሉ፡፡ የፀጉርን ቆዳ በሞቀ የኮኮናት ዘይት ማሸት ሴሎቹ እንዲነቃቁ ያደርጋል፡፡
4- እንቁላል መጠቀም
እንቁላል ነጩን ብቻ በመምታት ፀጉርን በመቀባት ፀጉርዎ ፈጣን እድገት እንዲኖረዉ ማድረግ ይቻላል፡፡ ፀጉርዎን እስከ ጫፉ ድረስ በመቀባት ጠንካራና ጤናማ ፀጉር እንዲኖሮዎት ያድርጉ፡፡
5- የኮክ ቅጠል
100 ግራም የኮክ ቅጠል በ1ሊትር ዉኃ ለ15 ደቂቃ ያህል መቀቀል፣ አዉርደን ለብ ሲል ፀጉራችንን በዉኃዉ መታጠብና ቆዳችንን በማሸት በላስቲክ ሸፍነን ከ1ሰዓት ቡኋላ በንጹህ ዉኃ ማለቅለቅ ለፀጉር እድገትን ያፋጥናል፣ የፀጉር መሳሳትን ይከላከላል፡፡
6- እሬት(ኦሊቬራ) ለፀጉር እድገት
1 የኦሊቬራ ቅጠል በመሰንጠቅ ዉስጡ ያለዉን ዝልግልግ ፈሳሽ በማዉጣት ፀጉራችንን እስከ ስሩ በማዳረስ መቀባት፣ ቆዳችንን ለጥቂት ደቂቃ ማሳጅ ማድረግ፣ ለ30-45 ደቂቃ ያህል በላስቲክ ሸፍኖ ማቆየት፣ ከዛ መታጠብ፡፡
ለፀጉር እድገት፣ ለፀጉር መነቃቀል እና መሳሳት እንዲሁም ለፎረፎር እሬት(ኦሊቬራ) መድኃኒት ነዉ፡፡
ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
@zena_science
@zena_science












