የደም ማነስ (Anemia)፡ ችላ ሊባል የማይገባው የጤና እክል
ሁሌ የድካም ስሜት ይሰማዎታል?
ትንሽ እንደተንቀሳቀሱ ትንፋሽ ያጥርዎታል?
እነዚህ ምልክቶች የደም ማነስ ሊሆኑ ስለሚችሉ ትኩረት ይሻሉ!
የደም ማነስ ማለት በሰውነታችን ውስጥ ኦክስጅንን የሚያጓጉዙት ቀይ የደም ሕዋሳት ወይም ሄሞግሎቢን ሲቀንሱ የሚከሰት ችግር ነው።
⚠️ ዋና ዋና ምልክቶች
▪️ ከባድ ድካምና የአቅም ማነስ
▪️ የቆዳ መገርጣት (Paleness)
▪️ ፈጣን የልብ ምት (በተለይ በእንቅስቃሴ ጊዜ)
▪️ የትንፋሽ ማጠርና ራስ ምታት
▪️ ትኩረት መሰብሰብ መቸገር
🔍 እንዴት ይከሰታል?
▪️ የአይረን (ብረት) እና የቫይታሚን ቢ12 እጥረት
▪️ ከፍተኛ የደም መፍሰስ (ለምሳሌ ከጨጓራ ቁስለት)
▪️ ሥር የሰደዱ በሽታዎች (እንደ ኩላሊት ሕመም)
▪️ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
✅ የመፍትሔ መንገዶች
▪️ በአይረን የበለጸጉ ምግቦችን (ቀይ ሥጋ፣ ምስር፣ ባቄላ) መመገብ
▪️ በቫይታሚን ቢ12 የበለጸጉ ምግቦችን (እንቁላል፣ ወተት) መመገብ
▪️ መንስኤ የሆኑ በሽታዎችን በአግባቡ መታከም
▪️ የአልኮል መጠጥን መቀነስ
▪️ የሕክምና ክትትል ማድረግ
👉 ማስታወሻ: እነዚህ ምልክቶች ካለዎት ትክክለኛውን ምርመራና ሕክምና ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።
@zena_science
@zena_science
5
1
1August 6, 2026 523 1