ዜና ሳይንስ 👁: post #3888 — TG.ME

የኑክሌር ፍንዳታ :ከአንድ ሚሊሰከንድ በታች የተነሳው ታሪካዊ ፎቶ

ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ከተነሱት አስገራሚ ታሪካዊ ምስሎች አንዱ የሆነው የኒውክሌር ፍንዳታ ፎቶግራፍ ሳይንሳዊ ሚስጥሮችን ይዟል።

ይህ ፎቶግራፍ በ1952 ዓ.ም በኔቫዳ ከተካሄደው የTumbler-Snapper የኒውክሌር ፍተሻ ተከታታይ አንዱ የሆነ ፍንዳታ ከተከሰተ ከአንድ ሚሊሰከንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተነሳ ነው። በዚህ ቅጽበት፣ በፍንዳታው የተፈጠረው የእሳት ኳስ ስፋት 20 ሜትር (66 ጫማ) ይደርሳል ነው የተባለው።

ፎቶውን ለመቅረፅ የተቻለው በ1940ዎቹ በሃሮልድ ኤጀርተን (Harold Edgerton) የተፈለሰፈው ራፓትሮኒክ (Rapatronic) ካሜራ በተባለ እጅግ ዘመናዊ መሣሪያ ነው። ይህ ካሜራ እስከ 10 ናኖሰከንድ (አስር ቢሊዮንኛ ሰከንድ) ድረስ ባለው አጭር የብርሃን መጋለጫ ጊዜ (exposure time) የኒውክሌር ፍንዳታውን ፈጣን ጊዜያት የማቆም ልዩ ችሎታ አለው።

በምስሉ ላይ በእሳቱ ኳስ ግርጌ በኩል የሚታዩት ስለታማ “እሾሆች” ወይም “ሾጣጣዎች” (spikes) “የገመድ ዘዴ” (Rope Trick Effect) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ የተፈጠሩት ቦምቡን ከታች የሚይዙት ገመዶች ወይም ኬብሎች በፍንዳታው ከፍተኛ ሙቀት በፍጥነት ተተነው ወደ ብርሃን በሚያመነጭ ትነት (vapor) በመቀየራቸው ነው። ይህም ሳይንቲስቶች የፍንዳታውን የመጀመሪያ ጊዜያት እንዲረዱ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል።

@zena_science
@zena_science
❤5
August 11, 2026 666