ሎሚ እና ጨው ለማይግሬን ህመም የመፍትሄ አማራጭ የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ-ገጽ ዘገባ እንደሚለው፣ ይህ ውህድ… — ዜና ሳይንስ 👁 — TG.ME

ሎሚ እና ጨው ለማይግሬን ህመም የመፍትሄ አማራጭ

የሄልዚ ላይፍ ላንድ ድረ-ገጽ ዘገባ እንደሚለው፣ ይህ ውህድ የራስ ምታት ህመምን በቶሎ ለማስታገስ የሚረዳው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦

1. የጨው ሚና (ሴሮቶኒን ሆርሞን)
ጨው ጭንቀትን በማስወገድ ደስታ እንዲሰማን የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተሰኘ ሆርሞን መመረትን ይጨምራል።

ጭንቀት ደግሞ ለከባድ የራስ ምታት ህመም (ማይግሬን) መነሻ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ በመሆኑ፣ የጨው መጠቀሚያው ይህንን መነሻ ለመቀነስ ይረዳል።

2. የአጠቃቀም ዘዴ

የሁለት ሎሚ ጭማቂ እና የተፈጨ የሎሚ ቅርፊትን ከሁለት ማንኪያ ጨው ጋር አድባልቆ በቀዝቃዛ ስፍራ ማስቀመጥ።

ከዚያም ከተወሰነ ውሃ ጋር ቀላቅሎ መጠጣት።

ይህ ውህድ በሶስት ደቂቃ ውስጥ ከህመሙ ለማገገም ይረዳል ተብሏል።

አስፈላጊ ማስጠንቀቂያ

ከፍተኛ የደም ግፊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ጨው ችግሩን ስለሚያባብሰው ይህንን ውህድ እንዳይጠቀሙበት ዘገባው አጥብቆ ይመክራል።

የማይግሬን መነሻ ምክንያቶች

ዘገባው ከባድ የራስ ምታት (ማይግሬን) ህመም እንዲከሰት የሚጠቅሳቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

🔹ጭንቀት

🔹አደንዛዥ እፆችን መጠቀም

🔹የምግብ እጥረት

🔹የሆርሞን አለመመጣጠን

🔹የመድሃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት

የራስ ምታት የሚከሰተው በአዕምሮ ውስጥ የሚገኙ ትልልቅ የደም ስሮች ሲያብጡና ሲሰፉ ነው። ይህ የደም ስሮች እብጠት በዙሪያቸው የሚገኙ ነርቮች የተለያዩ ንጥረ ነገሮች እንዲለቁ ያደርጋል። እነዚህ የተመረቱ ንጥረ ነገሮች የአዕምሯችን ለህመም ያለውን ስሜት ይጨምሩታል። ህመሙ ቀስ በቀስ የሚጨምር ሲሆን፣ ከእንቅልፍ ስንነሳ የሚበረታ ከሆነ ከፍተኛ የህመም ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል።

@zena_science
@zena_science
❤3👏1
August 8, 2026 576 8