ክራር በዓውደ ምሕረት ኪቦርድ፣ ድራም፣ ጊታር ሆኗል። ክራር ቤተ ክርስቲያን መዝሙር ከምታቀርብባቸው የዜማ… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

ክራር በዓውደ ምሕረት ኪቦርድ፣ ድራም፣ ጊታር ሆኗል

ክራር ቤተ ክርስቲያን መዝሙር ከምታቀርብባቸው የዜማ መሣርያዎች አይመደብም። የቤተ ክርስቲያን የዜማ መሣርያዎች ከበሮ፣ ጸናጽል፣በገና፣ መቋሚያ፣ ማሲንቆ በሚለው ዝርዝር ክራርን አናገኘውም። ይሁንና በተለምዶ ተለምዷል። በሥርዓት አውጪዎችና አስከባሪዎች ፊትም ቢሆን ያለ ክራር የሚቀርብ መዝሙር የለም ማለት ይቻላል። ከዚህም አልፎ በአንዳንድ የንግሥ በዓላት ወረብ እስከማጀብ ደርሷል። በሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ማኅበራት የሚቀርቡ የኅብረት መዝሙሮች በባለ አበል ግለሰቦች ከተዋጡ ሰነባብተዋል። አሁን ያሉ ህጻናት እና ታዳጊዎች የኅብረት መዝሙር ጣዕም የሚያውቁ አይመስለኝም።

አሁን ክራር ሁሉም ሆኗል። ክራር ፒያኖ፣ ክራር ጊታር፣ ክራር ኪቦርድ፤ ክራር . . . ወዘተ ሆኗል። አስቀድሞም እነዚህ መሣርያዎች የተከለከሉበት ዋናው ችግሩ ከመሣርያዎቹ ስያሜ ወይም ቅርጽ አይደለም - ከሚያወጡት ድምጽና የድምጽ ቃና እንጂ። ይኸውም ድምጻቸው ከመንፈሳዊ ሥርዓት እና ተመስጦ አውጥቶ ወደ ሥጋዊ ፌሽታ የሚወስድ ስለሆነ።

ክራር አሁን ሁሉንም ተክቶ በዓውደ ምሕረት ድምጻቸውን እየሰማን ነው። ከዓውደ ምሕረት የምንሰማው በክራር የተቃኘ የፒያኖ፣ ጊታር፣ ኪቦርድና ድራም ድምጽ እንጂ የመዝሙር ስንኞች አይደለም። ስንኞቹ ሳንሰማ በክራር ተመርተን ፒያኖ፣ ጊታር፣ ኪቦርድና ድራም ጋር አብረን እንጮኻለን - ይህንን ነው 'ምስጋና ነው ፤ ዕልል በሉ አመስግኑ" የሚሉን
👍1
August 19, 2026 89