ከሞት_ያነሰ_መኖር ሞቷ አይደለም ኃዘኗ እና ጭንቀቷ ማየት የሚያስጨንቀው እናት ሬሳዋን ተንተርሶ ከመተኛት… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

#ከሞት_ያነሰ_መኖር

ሞቷ አይደለም ኃዘኗ እና ጭንቀቷ ማየት የሚያስጨንቀው እናት ሬሳዋን ተንተርሶ ከመተኛት የማይሻል ሞት ንገሩኝ።

እናት ሞታ በአጽናኝ ተከቦ መቅበር የነበረ ነው። እናት ሞታ ያለ ቀባሪ እና ያለ አጽናኝ የእናት ሬሳ እያሸተቱ መቀመጥ ግን ከመሞት በብዙ ያንሳል።

አቃባሪም አጽናኝም አይኑር። አቅም እንዳይኖርህ የሕጻንነት አቅም፣ እሱን እንዳትታገል በጨካኞች የቆሰለ ገላ፣ ከዚህም አልፎ በራብ የጠወለገ ሰውነት ይዘህ የእናትን በድን በትል ሲወረር ከማየት የማይሻል የሞት ዓይነት አለን?

ሀገሬ እግዚአብሔር ይሁንሽ!
August 27, 2026 47