ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ስለ #መንፈሳዊ_ጉዞዎች - 1 ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ​በ379 ዓ.ም በተካሄደው… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ስለ #መንፈሳዊ_ጉዞዎች - 1

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ​በ379 ዓ.ም በተካሄደው የ146ቱ አበው የአንጾኪያ ጉባኤ ላይ በም*ን*ፍ*ቅና መወረሯ ይወራ የነበረውን የዓረቢያን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ገምግሞ ሪፖርት እንዲያቀርብ ተልኮ ነበር።

በፊልስጤምና በኢየሩሳሌም የነበረው የሥነ ምግባር ውድቀት በጎርጎርዮስ ላይ እጅግ አሳዛኝና ሕመም የበዛበት ስሜት ያሳደረበት በመሆኑ በእነዚህ ምክንያቶች ወደ ቅዱሳት ስፍራዎች የሚደረግ የንግሥ ጉዞን አልደገፈውም። በተለይም እንዲህ ዓይነቱ ጉዞ የሴቶችን ንጽሕና እና ቅድስና ለአደጋ የሚያጋልጥ በመሆኑ ለእነርሱ የበለጠ ጎጂ እንደሆነ ተናግሯል።

ቅዱሱ በደብዳቤው እንዲህ ይላል፦

"ወዳጄ ሆይ!

በደብዳቤህ ጥያቄ [ስለ መንፈሳዊ ጉዞ] ጠይቀኸኛልና ከእርሱ ጋር ለተያያዙት ነጥቦች ሁሉ በቅደም ተከተላቸው መልስ መስጠት ተገቢ ሆኖ ይታየኛል። ስለዚህ አራሳቸውን በፍጹም መንፈሳዊ ሕይወት መምራት የሚፈልጉ ሁሉ ትኩረታቸው ሁሉ ጊዜ በየወንጌል መለኮታዊ ቃላት ላይ ቢያደርጉ መልካም ነው። በየትኛውም ሥራ ላይ የሚሠሩ ሥራቸውን በሥርዓትን በሕግ እንደሚመሩ እና ያገኙትን ያልተስተካከለ ነገር እንደሚያቀኑ ሁሉ እኛም ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛና እንከን የለሽ መስፈርት ልንጠቀም ይገባል። መለኪያችንም የወንጌል የሕይወት መመሪያ ነው። በወንጌል መሠረት በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ልንመራ ይገባል።

አሁን እሁን ወደ ምንኩስና እና ወደ ተባሕትዎ ሕይወት ከገቡት መካከል ሳይቀር የጌታችን የሥጋዌ ሕይወት መታሰቢያዎች የሚታዩባቸውን የኢየሩሳሌም ስፍራዎች መጎብኘት የምንኩስናቸው ወይም ብሕትውናቸው እንዱ ተግባር ያደረጉ አሉ። ስለዚህ ይህንን በወንጌል መመሪያነት ማየት መልካም ነው። የወንጌሉ ቃሉ እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች እንድንጠብቅ የሚያዝ ከሆነ ትእዛዙ የጌታችን እውነተኛ ትእዛዝ እንደመሆኑ ልንፈጽመው ይገባል። ከጌታ ትእዛዝ ውጭ ከሆኑ ግን ለራሱ ግብረገብ ለመሆን የሚፈልግ ሰው እንደዚህ ዓይነት ጉዞ ለመፈጸም የሚያስገድደው ምን እንደሆነ አገባኝም።

ቅዱሳን ያላደረጉትን ወይም ወደ መንግሥተ ሰማያት ቀረብ ያሉ ሌሎች ሰዎች ያላደረጉትን ነገር ለማድረግ ለምን ትሞክራላችሁ? ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድን እንደ በጎ ሥራ አላዘዘንም። 'እነዚህን ቦታዎች የሚጎበኙ ሰዎች የሚያገኙት ጥቅም ምንድን ነው?' ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ በሥጋ እዚያ እየኖረ፣ በሌሎች አገሮች ከምንኖር ከእኛ ዘንድ እንደሌለ አድርገው ያስባሉን? ወይስ መንፈስ ቅዱስ በኢየሩሳሌም ሞልቶ ወደ እኛ [በሌላ ቦታ ወዳለነው] መምጣት እንደማይችል አድርገው ያስባሉን?... ቦታን መቀየር አምላክን ወደ እርስዎ አያቀርበውም። የትም ቦታ ብትሆን ነፍስህ እርሱ ሊኖርባትና ሊመላለስባት የምትችል ከሆነች ጌታ ወደ አንተ ይመጣል። ነገር ግን የውስጥ ሰውነትህ በተንኮል የተሞላ ከሆነ በጎልጎታ፣ ወይም በደብረ ዘይት፣ ወይም በትንሣኤው መታሰቢያ ስር ብትቆም እንኳ ክርስቶስን በውስጥህ ለመቀበል በእርሱ ማመንን ገና እንዳልጀመረ ሰው ያህል የራቅህ ነህ። በአንፃሩ እውነተኛዋ ቤተልሔም፣ ጎልጎታ፣ ደብረ ዘይት እና ትንሣኤ የሚገኙት እግዚአብሔር በልቡ ውስጥ ባለው ሰው ልብ ውስጥ ነው።"

ይቀጥላል

ምንጭ:-
Gregory of Nyssa. Writings of Gregory of Nyssa. SermonIndex.net, c. AD 395.
🙏1
August 28, 2026 44 1