የሰማይ_ደጅ ድንግል ማርያም ሆይ! አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በሩቅ ተመልክቶ የሰማይ ደጅ ሲል የጠራሽ… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

#የሰማይ_ደጅ

ድንግል ማርያም ሆይ! አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በሩቅ ተመልክቶ የሰማይ ደጅ ሲል የጠራሽ የመንግስተ ሰማያት መግብያ በራችን ነሽ፡፡ በር ከውጭ ወደ ውስጥ እንዲያስገባ አንችም ከውድቀት ወደ ድኅነት እንድንገባ ምክንያት ሁነሽናልና #የሰማይ_ደጅ እንልሻለን። ያዕቆብ "ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው" ብሎ የመለኮት ማደርያነትሽ ተናገር።
ያዕቆብ ያረፈባት ደግሞም መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያትን ስፍራ "የሰማይ ደጅ" ካላት እግዚአብሔር ልያድነን በወደደ ጊዜ (የዘመን ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ) በተገባ ንጽሕት ሁነሽ የተገኘሽ አንቺማ ይልቁን እንዴት ይገባሽ ይሆን? ሰውና እግዚአብሔር ያገናኘሽ #በር።

"እኔ ሕይወት ነኝ" ያለንንና ቅዱስ ዳዊት "መድኃኒት" ያለውን አስገኝታልናለችና "የሕይወት በር" እንላታለን። ዮሐ 11፡ 25፥ መዝ 118
መንግስተ ሰማያት ቅሉ የእግዚአብሔር ማደርያ ማለትም አይደል? ስለዚህ አንቺ የመንግስተ ሰማያት መግብያ በር ብቻ ሳትሆኝ በቁሙ #መንግስተ„ሰማያት ብንልሽ አልተሳሳትንም ለዘጠኝ ወር የእግዚአብሔር (በተለየ አካሉ ወልድ) መኖርያ ሁነሻልና። ለዚህም አይደል "ሁለተኛ ሰማይ" ብለን የምናወድስሽ።

የማርያም ሥጋዋ ከሰው ልጆች ሁሉ ሥጋ የተለየና የከበረ ነው። ለዘጠኝ ወር የክብር ጌታ መኖርያ ይሆን ዘንድ የተመረጠና የተቀደሰ ነውና፡፡ የአገልጋዩን የሙሴን ሥጋ ያከበረ አምላክ (ከብዙ ዓመታት በፊት ወደ መቃብር የወረደውን ሙሴ በደብረታቦር እንዲገለጥ አድርጓልና) የማርያምን ሥጋ በስብሶ ይቀር ዘንድ አይተወዉም፡፡ እርሱ ትንሣኤም አይደል? ዮሐ 11፡25

ስለዚህ ድንግል ማርያም #ተነስታለች_በክብርም_አርጋለች

የእመቤታችን ፍቅሯ በልቡናችን ይሳልብን አሜን፡፡
(16/12/2010 ዓ.ም)
🥰1
August 22, 2026 69