#በICU_ውስጥ_ያለው_የፖለቲካችን_ኑዛዜ
ፖለቲካችን ከተሰናበትነው ቆይተናል። ጨርሰን እንዳንቀብረው ጣሩ ረዘም እንጂ። አሁን ኑዛዜውን እያጨረሰ ነው።
"ሀገር መሥርቼ ሕዝብ እመራለሁ" የሚለን የፖለቲካ ልሂቅ ይህ ነው። በፈራረሰች ጎሬቤት "የምታማልል ሀገር እገነባልሃለሁ" የሚል። ነገር ግን በፈራረሰች ሀገርም ቢሆን ሀገር እንዴት እንደሚመሠረት ትንሽ ፍንጭ እንኳ የሌለው። Coffee house ላይ ቁጭ ብሎ የሚያወራው የልቡናው መሻት ሁሉ ፖለቲካ የሚመስለው ሀገር መሥራች። በአንድ ሰዓት ውስጥ ዐሥር እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ነገሮች የሚናገር አቋም አልባ። ፖለቲካ ቁማር ነው ከሚሉት ጋር ያለውን ሁሉ ጨርሶ አስረክዞ (አስይዞ) አየር ላይ የሚንሳፈፍ።
በነገራችሁ ላይ የምትቀርብበት ሚድያ መምረጥም አንድ የፖለቲካ ነው - ዘው ብለህ ሁሉም ጋር አይገባም።
1July 31, 2026 59