ወንጀልን_እንደ_የድል_ዜና ከመጀመርያ እስከ አጋማሽ 20ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የተካሄዱት አንደኛው እና ሁለተኛው… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

#ወንጀልን_እንደ_የድል_ዜና

ከመጀመርያ እስከ አጋማሽ 20ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የተካሄዱት አንደኛው እና ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች መነሻ ምክንያታቸው ስንፈትሽ ቅድሚያ የሚናገኘው #ብሔርተኝነት ነው።
በእነዚህ ጦርነቶች ከተዋጊና አዋጊዎች ይልቅ በብዛት የሞቱት ሲቪሎች (በጦርነቱ ምንም ዓይነት ሱታፌ ያልነበራቸው ሕጻናት እና ሴቶች) ናቸው። በተለይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሞቱ ሲቪሎች ከተዋጊዎቹ በ3 ዕጥፍ ይልቃሉ።

ዓለም ጉዳቱን አይቶ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት አሽቀንጥሩ በጣለው የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ ተቸንክረን የሲቪል ዜጎች ሞት ማስቀረት የሚንችል አይመስለኝም።
ዓለም "ለካ እንዲህ ነበርን" እያለ እንደ የታሪክ ዶክመንተሪ የሚያየን ይመስለኛል።

ወንጀልን የድል ዜና አድርጎ የሚያቀርብ የፖለቲካ ድውይነታችን ገና ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል።
August 20, 2026 82