እንዲህ_ሲሆን_ነው_ሀገር_የሚትሻገረው! ('ለአፄዎች ስስ ልብ አለህ' ያልከኝ ወዳጄ ስማማ!!) ​«በሰሜን… — Gebreab Hagos (ዘ-አብ) — TG.ME

#እንዲህ_ሲሆን_ነው_ሀገር_የሚትሻገረው!
('ለአፄዎች ስስ ልብ አለህ' ያልከኝ ወዳጄ ስማማ!!)

​«በሰሜን ከአክሱም በቀር ትግራይን በሙሉ ወደ ኢጣሊያ፤ አክሱምንና አሳብን ወደኛ፤ በምሥራቅ ከእንግሊዝና ከፈረንሳዊ ወሰን የምንገናኝበትን ዙሪያውን ያለውን አገር ሰጥተን ሐረርን ወደኛ፤ በደቡብ ባሌን፤ አሩሲን በዙዋይ ባሕር በኩል እስከ ማርጋሪታ ባሕር ያለውን አገርና በምዕራብ ያሉትን አገሮች በሙሉ ወደ ኢጣሊያ አድርገን የቀሩት አገሮች ወደ እኛ እንደጸኑ እንዲኖሩ፤ በሁሉም አገሮች ላይ ንጉሠ ነገሥቱ ለእኛ እንዲሆኑ፤ ወደ እኛ ለቀሩት አገሮች የእድሚኒስትራሲዮን ሥራ የሚሠሩና አማካሪዎች ከኢጣሊያ እንድንቀጥር፤ ይኸንንም ሐሳብ የተቀበልን እንደ ሆነ ብዙ ሚሊዮን ሊሬ ለመስጠት ነበር» በዚህ ዓይነት ስምምነትም ኢጣሊያ ፈትና ሳይሳካላት ቀረ።

​እንደገና በስደት ሳለን ሙሶሊኒ ሰው ልኮ «ግርማዊነትዎ በገንዘብ መቸገርን ሰምቻለሁና በፈቀዱት አገርና ሥፍራ ቤተ መንግሥት ገዝቼ ለግርማዊነትዎ ልስጥ፤ ከዚያም በቀር አንድ ሚሊዮን ጊኒ በወለዱ ከቤተሰብዎ ጋራ እስከ ዕድሜዎ መጨረሻ ያለ ሐሳብ እንዲኖሩ ልስጥ፤ በእርስዎ ምክንያት ኢትዮጵያን ለመያዝና ለማሳወቅ ስለተቸገርኩ ለቅቄያለሁ ብለው ይፈርሙልኝ» ብሎ ጠየቀ።

​«እኔ ላገሬና ለሕዝቤ ፍርድ ለመጠየቅ መጣሁ እንጂ አገሬን ለመሸጥ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ በኢትዮጵያውያን ደም በተነከረ ጊኒ አይደፈረሰም» ብለን መለስንለት። ይኸንንም ሐሳብ ያቀረበልን በመጋቢት ወር ፲፱፻፳፱ ዓ. ም. ላይ ነበር። ሁለተኛ ደግሞ ባመቱ «አንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሰጥቼ ካገርዎም ከፍዬ ልስጥዎት፤ መሠረቱን ከተቀበሉት ስላገሩ ክፍያ ድርሻዮ ጠበብኝ ሰፋኝ ለማለቱ ምንም አያከራክረን እንስማማበታለን» ብሎ ጥያቄ አቀረበልን።

ይህን ሁሉ የምዘረዝርበት ምክንያት ግፍ ለተሠራበት ሕዝብ ታሪክ የማይገኝበትን ስምምነት ምንም ያህል ብቸገር የማልቀበል መሆኔን ለመግለጥ ነው። ከሥጋዬ ችግር ይልቅ የበለጠ ለነፍሴ ነፃነት አስባለሁ።
መንገሥታት ሁሉ ለየጥቅማቸው በሚስማሙ መጠን እኛንም ከጥቅማቸው ግዴታ ውስጥ አስገብተው ከማይታረም ስሕተት ላይ እንዳይጥሉንና ወደው በሠሩት ሥራ ይህ ደረሰባቸው እንዳያሰኙን፥ ለጥፋት ወንጀለኛነታቸው ተካፋይ እንዳያደርጉን መጠንቀቅና አርቆ ማሰብ ነበረብን።

ሕይወቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ
ቀ/ ኅይሌ ሥላሴ
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ 2ኛ መጽሐፍ
👏1
August 6, 2026 101