ኢማም አልቡኻሪ ልክ በዛሬዋ እለት በ 60 አመታቸው ይህችን አለም በሞት ተለዩ!
ታላቁ ፐርሺያዊው ( ኢራናዊው) አሊም እና ሙሀዲስ ኢማም ሙሀመድ ኢብን ኢስማኢል አልቡኻሪ በኢስላም ውስጥ ሀዲስን በመሰብሰብና በመሰነድ እጅግ ወደር የለሽ ከሆኑ ሙሀዲሶች ቀዳሚው ናቸው።
ኢማም አልቡኻሪ የተወለዱት በ 810 በያኔዋ ኹራሳን በዛሬዋ ኡዝቤክስታ በምትገኘው ቡኻራ ከተማ ነው። የኢማም አልቡኻሪ ቅድመ አያት በርደዝበህ የዞራስተራኒዝም ወይንም መጁሳ ትልቅ የሀይማኖት አባት (ማጊ) የነበሩ ሲሆን አያታቸው አልሙጊራ ሀይማኖታቸውን ከመጁሳ ወደ ኢስላም በመቀየር መኖሪያቸውንም ቡኻራ ከተማ አድርገዋል።
የኢማም አልቡኻሪ አባት ኢስማኢል ግን ትልቅ አሊም እና በአብደላህ ኢብኑ ሙባረክ እና ማሊክ ኢብኑ አነስ ላይ የዲን ትምህርትን ጥንቅቅ አድርገው የተማሩ ነበሩ። አባታቸው በልጅነታቸው የሞተባቸው ኢማም አልቡኻሪ የአባታቸውን ፈለግ ተከትለው ገና በህፃንነታቸው ነው ኢልምን ማሳደድ የጀመሩት። እናታቸውና ታላቅ ወንድማቸው መካ ለሀጂ ይዘዋቸው ሲመጡ ደግሞ መንገዶች የበለጠ ተመቻቹላቸው። ለኢማም አልቡኻሪ የኢልም ጉዞ እናታቸው የማይተካ ሚና ነበራቸው። ኢማም አልቡኻሪ ሙሀመድ ኢብኑ ኢስማኢል መካ ከደረሱ በሗላ እዚያው ቀሩና ኢልምን ማካበት ጀመሩ። እዚያ እያሉ ነበር ቀዲያ አሶሀባ ወታቢኢን የፃፉት። ከዚያ ወደ መዲና በማምራትም ኢልም በመቅሰም አታሪኽ አልአክበርን ፅፈዋል።
ከዚያ በሗላ ኢማም አልቡኻሪ የኢልም ሀገሮች አልቀሯቸውም። ከባግዳድ እስከ ግብፅ ፤ ከኩፋ እስከ የመን ፤ ከበስራ እስከ ሶሪያ የሙስሊሙ የኢልም ማእከላትን በጠቅላላ በማዳረስ የነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሀዲሶች ሰበሰቡ።
ከነ ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ፤ የህያ ኢብኑ ሙኢን ፣አሊ ኢብን አል መዲኒ ወዘተ ኢልምን ቀሰሙ።
ኢማም አልቡኻሪን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር የሂፍዝ ተሰጥኦቸው ነበር። ኢማሙ ከ 600,000 በላይ ሀዲሶችን የሰበሰቡና የሀፈዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አጣርተው ሶሂህ የሆኑትን ብቻ ለይተው 7,275 ሀዲሶችን ብቻ በኪታባቸው አስተላልፈውልናል።
ያ ኪታባቸውም ከቁርአን በሗላ ያለው ትልቁ ኪታብ ተብሎላቸዋል
ኢማሙ ለኢልም የተሰጡ ለሀቀኝነት ብቻ የኖሩ ሙሀዲስ ነበሩ።
በሀዲስ ስብሰባ ጉዟቸው ከተፈጠሩ ነገሮች አንዱ ሲወራ በእጅጉ የሚደንቅ ነው።
እናታቸው ሀዲስን ከሀገር ሀገር ተንከራተው ሲፈልጉ እንዳይቸገሩ ብለው 15,000 ዲናር ሰጥታቸው ነበር። እናም በጀልባ እየተጓዙ ሳለ አንድ ይሄን ያክል ገንዘብ እንዳላቸው ያወቀ ሰው 15,000 ዲናሬን ይሄ ሰው ሰርቆኛል ብሎ ጮኸ። በዚህ ጊዜ ኢማሙ የያዙትን ገንዘብ ቀጠቅላላ ባህር ውስጥ ጣሉት ያገንዘብ የባህር ሲሳይ ሆነ።
ያ ቀጣፊ ሰውየ ደነገጠ። እንደት ይህን ሁሉ ገንዘብ ባህር ውስጥ ትጥላለህ አላቸው። እርሳቸውም የኔ በሆነ ገንዘብ ተከራክሬ ማስመለስ ብችልም ግና ሰርቆ ነበር የሚል ጥርጣሬ ሰዎች ዘንድ ከተሰማ ሀዲሶቼ ጥርጣሬ ውስጥ ይገባሉና ይህን አደረኩት አሉ ይባላል።
ኢማም አል ቡኻሪ አላህ ምድር ላይ ካመጣልን ሶጦታዎች አንዱ ናቸው!
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
Telegram
Seid Social
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

82
15
4September 1, 2026 6.7K 10 26