ዞህራን ማምዳኒ አሜሪካ አልተወለደም። በዘሩም አሜሪካዊ አይደለም። ሀይማኖቱ ሙስሊም ዘሩ ህንዳዊ ተወልዶ… — Seid Social — TG.ME

፨ ዞህራን ማምዳኒ አሜሪካ አልተወለደም። በዘሩም አሜሪካዊ አይደለም። ሀይማኖቱ ሙስሊም ዘሩ ህንዳዊ ተወልዶ ያደገው ዩጋንዳ ሲሆን አሜሪካ ገብቶ የአሜሪካ ዜጋ ሆኖ በፖለቲካው ዘርፍ ያደረገው የነቃ ተሳትፎና ለኒውዮርክ ከተማ ህዝብ ይዞት የቀረበው አስደናቂ ፖሊሲና ሀሳብ የኒውዮርክ ገዢ እንዲሆን አስቻለው። ዘሩም ብሔሩም ሀይማኖቱም ብቃቱን ደፍጥጦ ከአመራርነት አላስቀረውም። ኒውዮርካዊያን ከሀሳቡና ፖሊሲው እንጅ ከዘሩ ደንታ አልነበራቸውም!

፨ ቦሪስ ጆንሰን የኦቶማኑ ባለስልጣን አሊ ከማል የልጅ ልጅ ልጅ የሆነ ትውልደ ቱርካዊ ቢሆንም በእንግሊዝ ላይ የፖለቲካ ቁንጮ ሆኖ እንግሊዝን ከመምራት አልከለከለውም!

፨ ባራክ ኦባማ ከኬኒያ ዘሩ የሚመዘዝ የተወለደውም ኬኒያ ቢሆንም ከአሜሪካ ታላላቅ ፕረዚዳንቶች አንዱ ከመሆን ዘሩ አልከለከለውም!

፨ ሪሺ ሱናክ ዘሩ ህንዳዊ ቢሆንም የእንግሊዝ መሪ ከመሆን አልከለከለውም!

፨ ሷዲቅ ኻን ዘሩ ፓኪስታን ሀይማኖቱ ሙስሊም ቢሆንም ታላቋን የአለማችን ከተማ ለንደንን ከመመምራት አልከለከለውም። ለንደንም በጣም ስኬታማ ከሆኑ መሪዎቿ አንዷ አድርጋ ይዛዋለች።

፨ ሰርጌ ላቭሮቭ ዘሩ አርሜናዊ ቢሆንም የሩሲያን የውጭ ግንኙነትና ድፕሎማሲ በመምራት ምናልባትም ከፑቲን በመቀጠል የሩሲያ መልክ የሆነ በአለማችንም ካሉ ስል ድፕሎማቶች አንዱ ነው።

እንዲህ እንዲህ እያልን በሰለጠነው አለም ብቃት እስካለህ ድረስ መሪያቸው ሊያደርጉህ ፤ የኢኮኖሚ ማማ ላይ የቴክኖሎጂ መሪነትንም ሊያቆናጥጡህ ቅር እንደማይላቸው ማሳያ ነው።

የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ጂያንቶች 60% መሪዎቹ አሜሪካ ያልተወለዱ ዘራቸው ከሌላ የሚመዘዝ የቴክኖሎጂና የቢዝነስ መሪዎች ናቸው። አውሮፓ ብትሄዱ ካናዳ ፤ አውስትሪያ ኒውዚላንድ በአጠቃላይ የሰለጠነው አለም እንዲያ ነው። ብቃት ይኑርህ አንተንም ህዝብንም የምትጠቅም ሀገራቸውን የምታኮራ ሁን ከፍ አድርገው ይጠብቁሀል።

እኛ ሀገር እሳ!!??
ለማሰብም ይዘገንናል!

ያው ያልሰለጠነ ማህበረሰብ አንዱ መገለጫው በዘርና ብሔርተኝነት ልጓም መለጎም ነውና ሁሉም ነገር ላይ በዘር ነው የምትመዘነው!
ዶክተርነት በብሔር ኮታ ነው!
አመራርነት በብሔር ኮታ ነው!
ዲፕሎማትነት በብሔር ኮታ ነው!
የሀይማኖት መሪነት በብሔር ኮታ ነው!
አስቀዳሽ አሰጋጅ ኢማምና ቄሱም በብሔር ኮታ ሆነዋል!
የትም ተቀጠር ብሔር ካርድ ተመዞ ነው!

ሁለ ነገሩ በዘረኝነት የጠነባ ሀገር የጠነባን ህዝቦች የጠነባ ስርአት!
ደግሞ የሚያሳዝነው እየባሰብን ነው እየሄድን ያለነው!

አለም ሌላ የቴክኖሎጂ መራቀቅ ላይ እየተሽቀዳደመ ፤ በጣም ክህሎት ያላቸውን የትኛውንም ሰው የራሱ ለማድረግ እየታገለ እኛ እዚህ ዘር እየቆጠርን ከመገዳደልና ከመፎካከር የዘለለ ወይ ፍንክች!

አሁንማ ፀሀዩ መንግስታችን ትምህርትንም እየገደለልን ነው ስራንም እያጠፋልን ነው ኑሮንም አሪፍ አድርጎ እያስወደደልን ነው
ገና ዘር እየቆጠርን እንተናነቃታለን!

አቤት ቅዱስነታችን¡

https://t.me/EasyGift67bot?start=_tgr_PUw5w1sxZWRk

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
Telegram
Seid Social
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
❤69👍29😢9😁1🤔1💯1
September 3, 2026 3.8K 10 8