በሶማሊያ የመውሊድ ዝግጅት 1,538 ግመሎች ለሶደቃ ተዘጋጅተዋል።
ሶማሊያዊያን ይሄን ሁሉ ግመል ለሶደቃ አዘጋጅተው ወደ ቦታቸው ሲወስዱ የሚታየው ትእይንት የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀንን ትኩረት ስቧል።
ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የተወለዱበት ረቢኡል አወል ወር መግባቱን ተከትሎ በመላው አለም የሚገኙ ሙስሊሞች ወሩን በተለየ መልኩ ነብያችንን እያሰቡ ይገኛሉ። በተለያዩ የዝግጅት አይነቶችም እያሳለፉት ይገኛሉ።
የጎረቤታችን ሶማሊያዊያንም በዚህ መልኩ እየተዘጋጁ ነው።











