የውጭጉዳይ ሚኒስትር የዲፕሎማቲክ አታሼ ማስታውቂያ 100 አመልካቾችን እፈልጋለሁ ብሎ ማስታወቂያ አውጥቶ… — Seid Social — TG.ME

የውጭጉዳይ ሚኒስትር የዲፕሎማቲክ አታሼ ማስታውቂያ 100 አመልካቾችን እፈልጋለሁ ብሎ ማስታወቂያ አውጥቶ ከማመልከቻ መስፈርቶች አንዱ ብሔር ነው።
ብሔር የግድ ካልሞላችሁ የስራ ማመልከቻውን ማመልከት አትችሉም።

እንግዲህ ዲፕሎማቲክ አታሼ ሀገራችሁን በአለምአቀፍ መድረክ ወክላችሁ በወታደራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፤ ንግድና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከሀገራት እና አለምአቀፍ ተቋማት ጋር የምትሰሩበት ሀገራችሁን የምትወክሉበት ለሀገራችሁ መረጃና ጥናት የምታቀርቡበት ዘርፍ ነው።

እናም ይህ ዘርፍ እንኳ ከብሔር ጦስ አልተረፈም።
ብቻ የዚህች ሀገር ፖለቲካ የዚህች ሀገር ስርአት ግም ነው።ተስተካክሎ አያውቅም። የሀገሪቱን ጥቅም አስቀድሞ አያውቅም። የሀገሪቱን ውህደት አፋጥኖ አያውቅም!
ሁሌም ከፋፍሎ ለስርአቱ ማራዘሚያ እንደሆነ የሚቀጥል ግም ስርአት ነው ለመቶ አመታት የተዘፈዘፈባት።

ሀይማኖተኝነቷም ብሔርተኝነቷም ከመጥቀም ይልቅ ያደኸዪዋት ያቆረቆዟት ያነቀዟት የግፍና ክፋት መሳሪያ የሆኑባት ሀገር ተምሳሌት ነች።

ይህቺ ሀገር ግን ኤጭ!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍38❤15💔13🤔6
September 3, 2026 4.1K 14 9