በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እነዚህን አረመኔዎች ከሳኡዲ የፀጥታ ሀይል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር… — Seid Social — TG.ME

በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እነዚህን አረመኔዎች ከሳኡዲ የፀጥታ ሀይል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ በጣም የሚያስመሰግነው ትልቅ ሰስራ ነው።
እስካሁን ያ ልጁን እባክህን ለእናቴ አንድ ነኝ አትግደለኝ እያለ እየተማፀነ ያረደው አውሬና 5 ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ቲክቶክ ላይ እረደው ግደለው እያሉ ሞትን ሲነግዱ የነበሩ ከ 100 በላይ አረመኔዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንግዲህ ሳኡዲ ላይ የገደለ ፍርዱና ቅጣቱ ምን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነውና አንጀት ያርሳል። እንኳንም ፍርዳቸው ሳኡዲ ላይ ሆነ!
ይህ ሌሎች እንዲህ እየጨከንን እንቀጥላለን ማንም አይደርስብንም ለሚሉ ደም ጠጮች ትልቅ ትምህርት ነው።

በሳኡዲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ እንዲህ አይነት ጥረቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የንፁሀንን ህይወት እንዲታደግ የሁላችንም ጥሪ ነው!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍42❤18👏7🥰3🫡2
September 1, 2026 1.5K 9 1