ግን አሁን ላይ እንደኛ እንደ ሙስሊሞች አደብ ያጣ ስነምግባር የጎደለው አለ ወይ? ኧረ ተው እንኳን… — Seid Social — TG.ME

ግን አሁን ላይ እንደኛ እንደ ሙስሊሞች አደብ ያጣ ስነምግባር የጎደለው አለ ወይ?
ኧረ ተው እንኳን ከኢስላማዊው ከሰዋዊው የስነምግባር ሀዲድ እየወጣን ነው!
የሰዎችን ግለሰባዊ መብቶችን ሁሉ ጨፍለቀን አልፈን ስለሁሉም የግል ህይወት ካልፈተፈትን እያልን ነው!
ሰዎች የሚያገቡትን መምረጥ ያምረናል!
እኛ ራሳችንን የኢማን መስፈርት የኢማን ውሀልክ አድርገን ሌሎቹን እየለካን ነው!

ምላሳችን የሞተሰ ሰው እንኳ አያስቀምጥም!
መሻኣኾች ባለፉ ቁጥር ለምን አላህ ይማራቸው ትላላችሁ እያሉ ስንት አዛ የሚያደርጉ ምእመናንን አፍርተናል።
ባለፈው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር ኢድሪስ ሲያልፉ አላህ ይማራቸው እያሉ የፖሰቱትን ሁሉ በውስጥ እየገቡ አጥፉ ለርሳቸው አላህ ይማራቸው ማለት አይበቃም እያሉ ሲያስጠፉ የነበሩ ኡስታዝ ተብሎ የሚጠሩ በርካታ ሙተጦሪፍ ጥራዝ ነጠቆችን አይቼ በጣም ያሳዘነኝ ክስተት ነበር!
እነ ኢማም ዩሱፍ አልቀረዷዊ ሲናልፉ ይህንኑ ዘመቻ ከፍተው የነበሩ በርካቶች ነበሩ!
እነ ሸይኽ አቡኢስሀቅ አል ሁወይኒ ሲያልፉ በቃ ምናለፋችሁ ከጧኢፋቸው ውጭ ያለ መሻኢኽም ይሁን ሙስሊም በሞተ ቁጥር አላህ ይማራቸው አትበሉ እያሉ የፈትዋ መአት የሚያዥጎደጉዱ ስርአት አልባዎች እን። አሸን ፈልተዋል።

በሁሉም ሰው ህይወት ውስጥ ያገባናል ፤ ከሚያገባው ከምታገባው እስከ አመለካከቱ በእኛዋ ቀጭን መስመር ብቻ እንቅረፅለት የሚሉ ጀግኖች!

ተው ግን ተው ከዚህ ስነምግባር ዝቅጠት እንውጣ!

ዛሬ በሌላ ሰው ክብር ላይ ጥሰት የምታለማምዷቸው ጀማሪዎች ነገ እናንተኑ ይረማመዱባችሗል። እያየነው ያለነውም ይሄንኑ ነው!

ሙስሊም ሆነን ተሳዳቢ ፣ አነዋሪ ፣ ዋሾ ፣ መጥፎ ተናጋሪ ፣ ጨካኝ ፣ ፈራጅ ፣ የሰው ነውር አፈንፋኝ ፣ ሀሜተኛ ፣ የሰው ስም አጥፊ ፣ በማይመለከተን ሁሉ ጥልቅ የምንል ፣ አንደበታችን ያልተገራ መሆን ባልተገባን ነበር።

ነብያችን አለይሂ አሶላቱ ወሰላም እንደነገሩን የውመልቂያማ ላይ የመልካም ስየምግባርን ያክል ሚዛን የሚደፋ የለም። የኢስላም መልእክትና አላማም የሰው ልጆችን በስነምግባር ማነፅ ከመጥፎ ስነምግባርም መከልከል ነው።
ከዚህ የተለየ የለየለት የስነምግባር ጉድለት እያሳየን ከእኛ ውጭ ትክክለኛ ሙስሊም የለም ማለት ንፍቅና ነው!
ከማውራት መሆንን ማስቀደም ኸይር ነው። ለመሆን የሚጥር ደግሞ ከሌሎች ጉድለቶች ይልቅ የራሱ ጉድለት ላይ ቢዚ ይሆናል።

ለዚህ ነው ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም
طوبى لمن شغله عيبه عن عيوب الناس

ከሰዎች ነውር ይልቅ የራሱ ነውር እረፍት ያሳጣው ሰው ጀነት ምንኛ አማረችለት ያሉት!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
Telegram
Seid Social
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
❤71👍11🥰1🆒1
August 31, 2026 4.5K 18 6