የኢትዮጵያ ባህል እና ማንነት ስንል የኦሮሞውም ፣ የአማራውም ፣ የትግራዩም ፣ የሶማሌውም ፣ የአፋሩም ፣ የደቡቡም የሁሉም ባህልና ማንነት ውህድ ማለታችን ነው።
ኢትዮጵያ ከነዚህ ብሔሮቿ ማንነት ውጭ ሌላ ማንነት የላትም። አንድን ሰው ኢትዮጵያዊ የሚያስብለውም ከነዚህ ስብጥር ማንነቶቿ በአንዱ ሲወከል ወይንም የአንዱ ሲሆን ነው።
የአንዱ ብሔር ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አካል ነው። ብቻውን ግን አይደለም።
በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አካላት ከነዚህ ስብጥር ማንነቶቿ አንዱን ቢያንፀባርቁና ቢያሳዩ የወከሉትም ያንፀባረቁትም ከኢትዮጵያ ውህድ ማንነቶቿ አንዱን ነውና እነዚያ የኢትዮጵያ ወኪሎች ናቸው።
እያንዳንዷን ቅፅበት በመጠቀም የበለጠ ህዝብን ከህዝብ ለማራራቅ የበለጠ ለማጣላት የበለጠ በጥርጣሬ እንዲንተያይ ለማድረግ የሚዘምቱ አካላትን ተሰሚነት ማሳጣት ከሁላችንም የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው።
የኢትዮጵያ ማንነት የህዝቦቿ ማንነት እንጅ ሌላ አይደለም። እያንዳንዱ የህዝቧ ባህልም ኢትዮጵያዊነትን ይወክላል።
ይህች ልጅም ያሳየቺው የባህል ልብስ ከፍተኛ አድናቆትና ሙገሳን የሚገባት የሚያደርግ እንጅ የሚያስተቻት አንድ እንኳ ምክንያት የለም።
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

56
15
2
2September 5, 2026 4.1K 7 5