"ከዚህ በኋላ ክርስቶስን በገንዘብ የሸጠው ሰው ላይ አልፈርድም።በደካሞችና በሰካራሞች ልብ ውስጥ ምን እንዳለ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው።"
ከአንድ ሰዓት በኋላ ወደ ሆቴሉ ስመለስ ጨቅላ ህጻን ያቀፈች ወጣት አየሁ። ሕፃኑ ስድስት ሳምንት ቢሆነው ነው። በዚያ ቅፅፈት ነበር ህፃኑ ለመጀመርያ ጊዜ ፈገግ ሲል እናቱ ያየችው። እናትየዋ በጥልቅ ስሜት ደጋግማ ስታማትብ አየኋትና ጠየቅኋት።
"ፈጣሪ ከሰማይ ሆኖ ከልቡ የሚፀልይን አንድ ሃጢያተኛ የሚሰማውን ደስታ የሚያክል ሌላ ደስታ ቢኖር የህፃን ልጇን ፈገግታ ለመጀመርያ ጊዜ የምታይ እናት ልብ ውስጥ ያለ ደስታ ነው"አለቺኝ።
የወጣቷ ሴት ንግግር ጥልቅ ነበር። በውስጥ መላውን የክርስትና አስተምህሮ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪ እና በሰው ልጅ መካከል ያለውን የአባትና ልጅ የፍቅር ትስስር የሚገልፅ ነበር። በንግግሯ የክርስቶስን መሠረታዊ ሃሳብ መግለጿ ልቤን ነካው።
©Fydor ዶስቶቭስኪ 🖤📚








