የኦሾን በእኛ ሀገር የተተረጎመውን ትቼ ብቻ የውጭ መፅሐፍቶችሁን ከ14 በላይ አንብቢያለሁ። ከ20 ያላነሱም ኢንተርቪዎችሁን ደጋግሜ ተመልክቻለሁ። ይህን ስናገር ፉከራ ሳይሆን በ«Addiction» እና «Obsession» መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት ነው። የኦሾ ንጹህ ወይይት፣ ዲቤት እና ቀጥታ ንግግሩን ማዳመጥ ሱስ ሳይሆን መለከፍ ነበር የሆነብኝ። በተለይ ሲናገር በጣም መረጋጋት ብቻ ሳይሆን በቃላቶችሁ መጨረሻ ላይ የሚጠቀመው «እስስ» የሚለው የድምፅ ቃና አንድን ሰው ሂፕኖታይዝ የማድረግ ኃይል አለው። ኦሾ መፅሐፍ ጽፎ አያውቅም። ነገር ግን በአስርት አመታት ውስጥ ብዙ ኢንተርቪዎች ተደርጓል። ከዛ ኢንተርቪው ተወስዶ ከ700 በላይ መፅሐፍ በስሙ ተጽፏል። አሁን ላይ ግን በእሱ ስም የተጻፈ መፅሐፍም ሆነ ኢንተርቪው ማየት ካቆምኩ ወደሁለት አመት ገደማ ሊሆነኝ ነው። ቢሆንም በኦሾ ስም ከተጻፉት ብሎም እኔ ካነበብኩት የትኛው ህይወህትን ቀይሯል? ወይም አስተሳሰብህን አስፍቶታል? ተብዬ ብጠየቅ «Walking in Zen, Sitting in Zen» ብዬ በመለስኩ ነበር።
Walking in Zen, Sitting in Zen 📖 ሞትን የሕይወት ተቃራኒ ጠላት ሳይሆን የሕይወት የመጨረሻ ምልክት ወይም መደምደሚያ አድርጎ ይመለከተዋል። እዚህ ጋር መናገር የምፈለገው መፅሐፉ ሞትን ውደደዱ ወይም ሞትን ፈልጉ አይልም፤ ይልቅስ አንድ ሰው ሕይወትን በሙሉዓት ሲቀበል መሞትን እንደመጨረሻ እንግዳ ሳይሆን እንደ ተፈጥሯዊ እጣ ፈንታ ይቀበለዋል ነው የሚለን።
የመፅሐፉ ዋና ማዕከላዊ ትርጉም ሞትን መቀበል ነው። ይህም የሚጀምረው ህይወትን ከመውደድ ነው። ያ ሰው ሞት ሲመጣ እንደ ጠላት አይሸሸውም እንደ እንግዳም አይመለከተውም ብቻ በዝምታ ይቀበለዋል። በነገራችን ላይ ሰዎች ሞትን የሚፈሩት ሕይወታቸውን ስለሚወዱ ሳይሆን ቀናቸውን በቅጡ አጣጥመዋት ስለማይኖሩ ነው።
Walking in Zen, Sitting in Zen ውስጥ በአንድ ነገር ብዙ ነገሮችን ተረድቻለሁ። ሞት ከሕይወት የተለየች ጠላት አይደለችም። ለምሳሌ ወደቤት የሚያስገባን አንድ በር ብቻ ነው ያለው በዛ በር መልሰን ስንወጣ ሞት ይሆናል። እዚህ ጋር ነው ልዩነቱ የሚጀምረው። ሰዎች በበሩ በኩል ሲገቡ ያጨበጭባሉ፤ መልሰው በዛ በር ውጡ ሲባሉ ይሸሻሉ። ያ የሆነበት ምክንያት ሞትን ካለማወቅ የሚመጣ እንግዳ ስሜት ስላለብን ነው።
ያ እንግዳ የፍርሃት ስሜት ከልጅነታችን ጀምሮ የተማርነው ህይወትን የሚያሳጣ ስህተታችን ነው። ወላጆቻችን ሞትን ይፈራሉ፣ ጎረቤቶቻችንም ይፈሩታል፣ ማኅበረሰቡ በጠቅላላ ይፈራዋል እኛም ፍርሃቱን እንደ ውርስ እንቀበለዋለን። የትም ቦታ ብንሄድ ስለሞት ማውራት የተከለከለ ቃል ሆኖ እናገኘዋለን።
ኦሾ ሌሎች እንደሚሉት የህይወት ተቃራኒ ሞት ሳይሆን ወሲብ ነው የሚል አስተሳሰብ አለው። ወሲብ እና ሞት የሕይወት መጀመሪያ እና መጨረሻ ናቸው። ሁለቱም በዝምታቸው ውስጥ ጠፍተዋል ይለናል።
በመጨረሻም መፅሐፉ ሊናገር የሚወደው አንድ ነገር ቢኖር፤ ሞትን ማስታወስ ሕይወትን መጥላት አለመሆኑን ነው። በተቃራኒው ሞት እንዳለ ማወቅ የዛሬን ቀናችንን የበለጠ ዋጋ እንዲኖረው ወይም እንድንሰጠው ያደርገናል። ሕይወት መጽሐፍ ከሆነች፣ ሞት የመጨረሻው ገጽ ነው። የመጨረሻው ገጽ ስላለ ብቻ ተበሳጭተን መጽሐፉን አንወረውረውም፤ ይልቅስ እስከምንረዳው ድረስ ገጾችሁን በጥንቃቄ እናነባለን። ያለመጨረሻውም ገፅ መፅሐፉ ትርጉም አልባ አልያም ያልተሟላ ነው የሚሆንብን።
ታላቅ ጥበብ ማለት ሞትን ማሸነፍ አይደለም፤ ታላቅ ጥበብ ማለት ሞት እንደሚመጣ እያወቅን ሕይወትን በሙልዓት መኖር መቻል ነው። ምክንያቱም የሕይወት ውበት ለዘላለም መቆየቷ ሳይሆን፤ አንድ ቀን እንደምታልቅ እያወቅን አሁናችንን ማጣጣም ነው። እስቲ ከመፅሐፉ የተመቸኝን አንቀጽ ላጋራችሁና ልሰናበት።
«Whenever death comes he hugs death. he embraces death, he welcomes death, he receives death as a guest. To the man who has not known what life is, death is an enemy; and to the man who knows what life is, death is the ultimate crescendo of life. But everybody is afraid of death; that too is contagious. Your parents are afraid of death, your neighbors are afraid of death. Small children start getting infected by this constant fear all around. Everybody is afraid of death. People don’t even want to talk about death.
There have been only two taboos in the world: sex and death. It is very strange why sex and death have been the two taboos not to be talked about, to be avoided. They are deeply connected. Sex represents life because all life arises out of sex, and death represents the end. And both have been taboo don't talk about sex and don’t talk about death!»
Source፦Walking in Zen Sitting in Zen 📖
@Armemo_offical




