@Imagination_officially · 7.7K subscribers
D𝚊𝚛𝚔 🌃 % S𝚞𝚗𝚜𝚎𝚝 🎴
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/Imagination_officiallyIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created November 23, 2018per Telegram
We have been tracking it since August 14, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
የአብዛኛው ተቀጣሪ ትልቁ ፍላጎት ቀለል ያለ በሽታ ቢይዘኝ ብሎ መመኘት ነው። በሽታው ካንሰር እና አስፈሪ አደጋ አይሁን እንጂ እንደጉንፋን፣ ብርድ ወይም መጠነኛ ትኩሳት ብቻ ለሶስት ቀናት እቤቱ የሚያርፍበት የሲክሊፍ ፈቃድ ማግኘት ነው ዋናው እቅዱ።
እነሆ ክብሯን ሆይ ይሄ የሰው ልጅ ሙሉ ለሙሉ የወደቀበት ጊዜ ማሳያ ነው። ልጅ እያለን ካመመን ትምህርት ቤት ከመቅረት ጀምሮ በቤተሰብ ትኩረት እስከ ማግኘት የተለያየ እንክብካቤ ውስጥ እንገባለን። ከአመታት በኋላ አድገን እራሱ ይህ ባህሪ አለቀቀንም።
ብቻ ዘመኑ ዘመነኛውን ሰው መስሏል። ዛሬ ላይ ህመም ከጤና የበለጠ ማራኪ እየሆነ መጥቷል። ምክንያቱም ጤነኛ መሆን ማለት ጠዋት ሁለት ሰዓት ላይ ስራ ቦታ መገኘት አለብህ የሚል ማስጠንቀቂያም ጭምር ነው። ያ ሰው በስራ ቦታ ተገኝቶ ለ9 እና 10 ሰዓታት ደፋ ቀና ማለቱ ምንም አይነት አዲስ ነገር እያመጣለት አይደለም። በርግጥ ሰራተኛው መታመም ሳይሆን በወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማው አልጋው ላይ የመቆየት መብት እንዳለው የሚያረጋግጥበት ወረቀት ነው የሚፈልገው።
በትንሹም ሰዋዊ አስተሳሰባችንን መቀየር ያልቻልን እንደምኞታን ቢደረግለን የፈጠነ የምንጠፋ ፍጡሮች ነን። ለነገሩ ዘመናዊው የሥራ ሥርዓት እራሱ ዕረፍትን ለታካሚው ብቻ የሚገባ ልዩ መብት አድርጎ አጽድቆታል። ጤነኛው ግን በየቀኑ ወዝና ላቡ እስከመጨረሻው መታለብ፣ ጊዜው እና ጉልበቱን ማባከኑን ማረጋገጥ አለበት። ታድያ ግን በዚህ አካሄድ ህይወቱን ለገንዘብ መስዋት አድርጎ ቢያልፍ፤ ቀሪ ህይወቱ ግን ያለገንዘብ ጡረተኛ ሆኖ የሚያበቃበት ሌላኛው የኪሳራ ጅማሮ ነው።
አብዛኛው የኢትዮጲያ ሰራተኛ ህመም ሲሰማው «በዚህ ስራ እንዲህ ተጨናንቄ እስከመቼ?» ከማለት ይልቅ ለእራሱ በሹክሹክታ እንዲህ ማለት ይቀናዋል፦«ነገ የፈጠነ ሃኪም ቤት ሄጄ ሲክሊፍ አጽፋለሁ። ከዛ ምርጥ የሆነ ቀን በቤቴ ማሳለፍ ነው!» 🤦🏽

3 advertisers placed 3 creatives in this channel · est. CPM $1–5.