#ቪንሰንት_ቫን_ጎህ
_
እብዱ አርቲስት ይሉታል፣ ስዕሎቹንም የተረበሸው አእምሮው ምስላዊ መገለጫ። በርግጥ አይፈረድባቸውም። አንድ ዓመት ያህል በአእምሮ ህሙማን ሆስፒታዎል አሳልፏል። ምርጥ የሚባሉትን ስዕሎቹን የሠራው በዚህ ሆስፒታል በነበረው ቆይታ ነው። በዚህም ጥቂት የገባቸው ማበዱን አይቀበሉም። እንደውም የላቀ የንቃተ ህሊና ደረጃ ላይ ነበር ብለው ያምናሉ።
ሥራዎቹ በወቅቱ ለነበሩ የጥበብ እኩዮቹ ፍፁም እንግዳ ነበሩ። ነገሮችን በማናውቃቸው መልኩ ነበር የሚያስቀምጠው። በሆስፒታል በነበረው ቆይታ ከሳላቸው ስዕሎች መካከል አንዱ ሽክርክሪት ቅርጽ ያላቸው የከዋክብት ክምችቶችን ነበር (ምስሉን ይመልከቱ)። ''ይህ ፍፁም እብደት ነው፤ እንዲህ አይነት የከዋክብት ክምችት የት አለ?'' ተባለ። ፊዚክስ እዚ እውቀት ላይ ለመድረስ 50 ተጨማሪ አመታት አስፈልጎታል።
ቫን ጎህ ከልቡ ሰዓሊ ብቻ አልነበረም፣ ጠቢብም ጭምር እንጂ። ምፀቱ ግን ወዲህ ነው። በህይወት ሳለ ከጥቂት ስዕሎች በስተቀር መሸጥ አልቻለም። እነዚህንም ስዕልሎች የገዙት አጎቱና ወንድሙ ናቸው። ሲሞት እንኳን፣ የገዛ ጓደኞቹ ጭምር ስዕሉን ቤታቸው ውስጥ መስቀል አልደፈሩም። መሳቂያ መሆን አልፈለጉም።
_
© Ja liberity













