#«ሴት አይደለሽም»
በሚል ከእግር ኳስ ሜዳ መገፋቷን መሳይ ተመስገን ተናገረች
በሴቶች ስፖርት ዘርፍ ከችሎታና ከሙያዊ ብቃት ይልቅ የመልክና የጾታዊ መግለጫዎች ተፅዕኖ የጎላ ፈተና መሆኑን የሚያሳይ አዲስ ገጠመኝ ይፋ ሆኗል።
ወጣቷ የእግር ኳስ ተጫዋች መሳይ ተመስገን (ደሰቄ) በቅርቡ በ«ሰባተኛ ፖድካስት» ላይ በቀረበችበት ወቅት እንደገለጸችው፣ ለአካባቢውና ለስፖርቱ የነበራት ጥልቅ ፍቅር በፆታዊ አመለካከቶች ምክንያት መገደቡን ተናግራለች።
«ሴት አይደለሽም፣ ወንድ ትመስያለሽ» በሚሉ ምክንያታዊ ባልሆኑ አስተያየቶች ከምትወደው የስፖርት ክለብና ከሜዳ እንድትርቅ መደረጓን ገልጻለች።
• በስፖርቱ ውስጥ ያሳለፈችው ከፍተኛ ፈተና ከእግር ኳስ ህልሟ እንድትገፋና የስፖርት መንገዷ እንዶታጎል ማድረጉን አብራርታለች።
ይህ አጋጣሚ በሴቶች ስፖርት ዕድገት ውስጥ ከችሎታ ይልቅ የሚሰነዘሩ ውጫዊ አስተያየቶች የበርካታ ታላላቅ ተቪዥኖችና ተሰጥኦዎች ማደናቀፊያ እየሆኑ መምጣታቸውን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

24
6
4
4September 2, 2026 3.7K 6