በደሴ ከተማ በሚሊዮን ብር የሚገመት የመሠረተ ልማት ንብረት ተያዘ
በደሴ ከተማ በተደጋጋሚ የመብራት ትራንስፎርመርና የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት እቃዎችን ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከተዘረፉ ንብረቶችና ከግብረአበሮቻቸው ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ጋር በመቀናጀት ባካሄደው የምርመራ ሥራ፣ በአንድ ግቢ ተደብቀው የነበሩ በሚሊዮን ብር የሚገመቱ ትራንስፎርመሮችና የቴሌ እቃዎች ተይዘው ለማስመለስ ተችሏል።
የደሴ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያና የፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች፣ የምርመራ ሥራው በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፣ ለስኬቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ የፀጥታ አካላትና ማህበረሰቡ ምስጋና አቅርበዋል።

25
4September 4, 2026 2.4K 1