ህወሃት የፌደራል መንግስትን በድሮን ጥቃት ሲከስ የአላማጣ ባለስልጣናት ደግሞ ህወሃትን ወቀሱ ህወሃት የፌደራል… — Mehal media — TG.ME

ህወሃት የፌደራል መንግስትን በድሮን ጥቃት ሲከስ የአላማጣ ባለስልጣናት ደግሞ ህወሃትን ወቀሱ
 
ህወሃት የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት በሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው ሲል የከሰሰ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የህወሃት ታጣቂዎች የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ወደ ወታደራዊ ካምፕነት ቀይረዋል የሚሉ የአካባቢው ሪፖርቶች መውጣታቸውን ዶቼ ቬሌ  ዘግቧል።
 
የህወሃት ቃል አቀባይ ሚካኤል አሰግዶም በድሮን እና በሚግ ተዋጊ አውሮፕላኖች የታገዘው የአየር ጥቃት በአምስት ዞኖች በሚገኙ የህዝብ ተቋማት ላይ ማረፉን የገለጹ ሲሆን፣ በሰሜን ምዕራብ ዞን ደጀን ከተማ የሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ መውደሙን፣ እንዲሁም በእንደርታ እና በራያ አዘቦ አርሶ አደሮችና የመኖሪያ መንደሮች መመታታቸውን ጠቅሰዋል።
 
ይሁን እንጂ ከአላማጣ ከተማ የተገኙ አንድ የቀድሞ የአካባቢው ባለስልጣን ለዶቼ ቬሌ በሰጡት ተቃራኒ መረጃ፣ የህወሃት ኃይሎች አራት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በአላማጣ የሚገኙ ስምንት ትምህርት ቤቶችን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እና የማዘጋጃ ቤት ህንፃዎችን በአሁኑ ወቅት ወደ ታጠቁ ወታደራዊ ይዞታነት እና መፈጠሪያነት ቀይረዋቸዋል ሲሉ ከሰዋል።
❤17👍5
September 4, 2026 3K 1