በአርባያ በለሳ ታጥቀው ሲዘርፉ በነበሩ ፅንፈኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አርባያ በለሳ አብዬ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ታጥቀው ሲዘርፉና ህብረተሰቡን ሲያሰቃዩ የነበሩ የፅንፈኛ ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰዱን የ10ኛ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አሰጋ አከለ ተናግረዋል።
እንደ ክፍለ ጦር አዛዡ ንግግር በቀጠናው እየተሽሎከሎኩ በነዋሪው ላይ እንግልት በማድረስ ሰላም ይነሱ የነበሩ የፅንኛው ቡድን አባላትን ለማጥፋት ድንገተኝነትን በመጠቀም መምታት መቻሉን ገልፀዋል።
የሀገር አፍራሹ ፅንፈኛ ቡድን የግል ጥቅማቸውን ለማስከበር በዘረፋና በእገታ ተግባር ተሰማርተው ሰዎችን ሲያሳድዱ በመቆየታቸው የክፍለጦሩ ሠራዊት በተጠና መልኩ በመሰማራት ብሬን፣ክላሽ፣ ኋላ ቀር መሳሪያ፣ በርካታ ቁጥር ያለው ቦምብና የክላሽ መጋዘን እንዲሁም ሎጀስቲካዊ ቁሳቁስ ማመረካቸውን አብራርተዋል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
10
4September 5, 2026 2.2K


