ጣሊያን ግብፅና ኢትዮጵያን ለመሸምገል ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች ጣሊያን በዓባይ ውኃ ውዝግብ ዙሪያ በግብፅ እና… — Mehal media — TG.ME

ጣሊያን ግብፅና ኢትዮጵያን ለመሸምገል ፈቃደኛ መሆኗን ገለጸች

ጣሊያን በዓባይ ውኃ ውዝግብ ዙሪያ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ውይይት ለማቀናጀት ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች። ሁለቱ አገሮች ዓለም አቀፍ ሕግን ጠብቀው በሰላማዊ መንገድ ፍትሃዊ መፍትሔ ላይ እንዲደርሱም አሳስባለች።

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ይህንን ሐሳብ ያነሱት ከግብፅ አቻቸው ጋር በግብፅ ኤል አላሜይን ከተማ ሐሙስ ዕለት ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

ግብፅና ኢትዮጵያ ከተስማሙ ሮም አስታራቂ በመሆን ውይይቱን ማገዝ ትችላለች ያሉት ሚንስትሩ፣ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ጥሩ ግንኙነት ችግሩን በሰላም ለመፍታት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
❤18👎17👍11👻3
September 4, 2026 2.6K 2