እግዚአብሔር ያፅናናል ቀናም ያደርጋል! ...ብዙ የጭንቅ ቀኖች እና የእንባ ለሊቶች ለነፍስ ክሳት ለመንፈስ… — Gilgal~ጌልገላ ለኢትዮጵያ🇪🇹 — TG.ME

እግዚአብሔር ያፅናናል ቀናም ያደርጋል!

...ብዙ የጭንቅ ቀኖች እና የእንባ ለሊቶች ለነፍስ ክሳት ለመንፈስ መጠውለግ ለስጋ ጉስቁልና ሰበብ የሚሆኑ እንደደራሽ ውሃ እና ድንገት እንደሚመጣ ጎርፍ የመጣውን እግዚአብሔር ዞር በል ሲል እንዳለፈ ውሃ መሄዱስ ግዴታው አይደል? በቃዴስ በረሃ ከረሃብ እና ከጥም ይልቅ የናፈቅነው መገኘቱ አሰንብቶን ፤ በአውላላ ሜዳ ላይ ድንጋይን ተንተርሶ በተኛበት የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን አይቶ ይህስ የሰማይ ደጅ ነው እንዳለው ሆኖልንም ጭምር እንጂ እስኪያልፍ የማያለፋ ምን አለ? አንድ ቀን በእግዚአብሔር  ጊዜ በተፅናናንበት መፅናናት ሌሎችን እንድናፅናና ዘንድ የእውነት አንድ ቀን እንስቃለን! ነፍሳችን መፅናናትን እንቢ እስክትል ድረስ ባዘነችበት ጉዳይ አምላካዊ መልስ ይሰጣል ውብም ያደርጋል!
         
    በእግዚአብሔር ቀን ቀናችን ውብ ይሆናል!

የእውነት የእግዚአብሔር መጽናናት አመሻሽ ይሁንላችሁ💪
@everthingspossible
ሁሌም የአዕምሮና የመንፈስ ስንቅ!
👍1
August 25, 2026 450