በእድል ካልሆነ በአምላክ ሞክረው ዩኒቨርሱ የሚሰራው በእርሱ ህግ ነው!
አምላክህ ቀን ከለሊት ቢሰራልህም አንተ ካልሰራህ ምንም አይሆንም ወፍ የለም። ሲፈጥርህ እንደራሱ ነፃ የሆነች ነፍስን በሰውነትህ አኖረ። ፈጣሪ ሁሉን ነገር መቆጣጠር ቢችልም ያንተን ነፍስ ግን ላንተ ቁጥጥር ትቷል። ዋጋህ እጅግ ትልቅ ነው። የንጉሶች ሁሉ ንጉስ ልጅ ከመሆንም በላይ ነው።
ይህ ካልገባህ ግን ነገር ይበላሻል።
ከሁሉ አስቀድመህ ነፍስህን እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ተማር። ያንተ ነፍስ ከአምላክ ባህር በረከቶችን የምትጨልፍ ልዩ መሳርያ ናት። ባለማወቅ ግን እርግማንም ልትጨልፍ ትችላለች። ነፍስህን በጥበብ መጠቅም ካስቸገርህ ለእርሱ መንፈስ አስገዛት። ያንተ ፈቃድ በእኔ ላይ ይሁን!" በለው የሚገባህንም ይስጥሃል።
መልካም የሥራ ቀን ተመኘሁ💪
@everthingspossible
ሁሌም የአዕምሮና የመንፈስ ስንቅ!

