Gilgal~ጌልገላ ለኢትዮጵያ🇪🇹: post #3955 — TG.ME

ስለእግዚአብሔር ማውቅ እግዚአብሔርን ማወቅ አይደለም። ስለእግዚአብሔር ማወቅ መረጃ ሲሆን እግዚአብሔርን ማወቅ መንፈሱን መቅመስ ነው።

በሐይማኖትህ የቱንም ያህል የተከበርህ ቄስ፣ሼክና ፓስተር ብትሆንም ስለእግዚአብሔር ማውቅ ብቻ ግን አያድንህም መንፈሱን ቀመስህ ማንነቱን ተላብሰህ ነፃ ካልወጣህ እምነትህ የውሽት ይሆናል።

አስታውስ ስለምግቡ ማወቅ ምግቡን መብላት አይደለም። ምግቡን በልተህ ስትጠግብ ሌላ ምግብ አያሳስብህምብ አየህ? አምላክህንም በልተህ ስትጠግብ ከእሱ ውጪ ሌላ ነገር አያስጨንቅህም። የአለም ነገር ሁሉ ከእግርህ በታች ይሆናል።

አምላክ የዩኒቨርሱ ምርጥ ምግብ ነው። ሰላም፣ ደስታ፣ ውበት፣ ሀብትና ህይወትን ለፍጥረት ሁሉ ይመግባል። ጥያቄው ግን አንተ አምላክን ቀምሰዋል? መንፈሱን ነክተሃል(ቴስት) አድርገዋል?

ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ጨለምተኝነት፣ ባዶነት፣ ራስን መጥላት የአምላክን የመንፈስ ምግብ ያለተመገቡ ሰዎች መገለጫዎች ናቸው። የሰው ልጅ በእንጀራና በዳቦ ብቻ አይኖርም። የእግዚአብሔርን መንፈስም በመመገብ ጭምር እንጂ።

የተባረከ ቀን ተመኝንላችሁ💪
@everthingspossible
ሁሌም የአዕምሮና የመንፈስ ስንቅ
👍8❤2🙏1
August 21, 2026 521 1