የአመራር ብቃትን ማሳደግ፣ በመረጃና በማስረጃ የሚመራ ተቋም መገንባት እና ተጠያቂነትን ከተቋማዊ ነፃነት ጋር አስተሳስሮ ማስፈንና ማስቀጠል የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ዋነኛ የሪፎርም ትኩረት መሆኑ ተገለጸ፡፡
-------------------- // ---------------------
(ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን፣ ከአሪዞና ዩኒቨርሲቲ እና ሽያሾኔ ተቋም ጋር በመተባበር የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች አቅም ግንባታ፣የፖሊሲ ጥናቶች ውጤት እና አመታዊ የሥራ አፈጻጸም ላይ የሚመለከታቸው የባለድርሻ እና አጋር አካላት የተሳተፉበት አውደ-ጥናት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አውደ-ጥናቱን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የአመራር ብቃትን ማሳደግ፣ በመረጃና በማስረጃ የሚመራ ተቋም መገንባት እና ተጠያቂነትን ከተቋማዊ ነፃነት ጋር አስተሳስሮ ማስፈንና ማስቀጠል የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ዋነኛ የሪፎርም ትኩረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለነገዋ ኢትዮጵያ የሚገባትን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መፍጠር የአውደ-ጥናቱ ዓላማ መሆኑን ጠቅሰው በከፍተኛ ትምህርት አመራሮች አቅም ግንባታ፣ በተለያዩ የፖሊሲ ጥናቶች ውጤት እና በአመታዊ የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት የሚካሄድ መሆኑም ተጠቅሷል።
በአሁኑ ወቅት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ቁጥር ከማሳደግ ይልቅ ያሉንን ተቋማት ጥራት እና አግባብነት ወደአላቸው ተቋም ማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው አንድን ዩኒቨርሲቲ ስናሻሽል ተቋሙን ብቻ ሳይሆን የብዙ ሺህ ወጣቶችን መጻኢ ዕድል እያሻሻልን መሆኑን ከግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18V
August 31, 2026 25.3K 11



