📢 ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ተመዝግባችሁ በአመራረጥ ሂደት ቅሬታ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎችን መልምሎ ማሳወቁ ይታወሳል። በአመላመሉ ዙሪያ ቅሬታ ያላችሁ ተመዝጋቢ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ (https://sbs.moe.gov.et/apply) በመግባትና complaint የሚለውን አማራጭ በመጫን ቅሬታችሁን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
August 31, 2026 26.8K 255