ማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ። ትምህርት… — Ministry of Education Ethiopia — TG.ME

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁና ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ መለያ ኮዳችሁን ( Reference Number) በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።

በተጨማሪም ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ፈተና የሚሰጠው በበየነ መረብ (online) ስለሆነ የሚቀርባችሁን የፈተና መስጫ ማዕከል በዛው ሊንክ በመግባት መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የሙከራ ፈተና እሮብ ነሃሴ 27/2018 የሚሰጥ ሲሆን ዋና ፈተናው ነሃሴ 28 የሚሰጥ መሆኑ አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።
August 30, 2026 34.1K 382