በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈጸሙ የሙስና እና የስነ-ምግባር ግድፈቶችን ተጠያቂነትን በማስፈንና የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ።
በትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርስቲ የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
------------------------ // -------------------------
(ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚፈጸሙ የሙስና እና የስነ-ምግባር ግደፈቶችን ለመከላከል ተጠያቂነትንና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ተጠያቂነትንና የአሰራር ስርዓትን ከመገንባት ባሻገር በመዋቅር ፣ በአሰራርና በሰው ሃይል ስምሪት ነገሮችን መለወጥና ማስተካከል እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገንዘብና ንብረት ሙስና ውጪ የተማሪ ምደባን ጨምሮ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ ቀድሞ ያልነበሩ አዳዲስ የሙስና ስጋቶች መኖራቸውንም ክቡር አቶ ኮራ ጠቁመዋል።
በመሆኑም የዩኒቨርስቲ የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚዎች በምሉዕነት የህዝብና የጋራ ጥቅሞችን በማስቀደም የትምህርት ጥራት ጸር የሆነውን ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በጽናት መታገል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BqyZxFCk6/




















