ቡጢ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
22፥11 ከሰዎች በጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን የሚያመልክ ሰው አለ። وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ
"ቡጢ"Boxing" ማለት "አምስት ጣቶችን በማጠፍ እና በመኮርመት ፊት ላይ ድብደባ ማሳረፍ" ማለት ነው፥ ቡጢ ከሥነ ጥበብ"Art" ቢሆንም ሥረ መሠረቱ ግን ዐረማዊ ልማድ"Pagan Custom" ነው። የሮማዊ የትግል፣ የድብድብ፣ ጦርነት አምላክ "ማርስ"Mārs" ሲባል የእርሱ ሥነ ጥበብ "የማርስ ሥነ ጥበብ"Martial art" ተብሎ ይታወቃል፥ ይህ የዐረማዊ ልማድ ከዛ ጀምሮ ዛሬ ላይ በእያንዳንዱ ሕይወት ውስጥ እንደ ጤናማ ስፓርት መታየቱ ማፈር እና መክሰር ነው። ውጪው የትጉኅ እና የታታሪ ሰው መገለጫ ቢመስልም ውስጡ ግን መብረድ እና መንደድ ያለበት ስሜታዊ ጉዳይ ነው፥ በዲኑል ኢሥላም ሰውን በቡጢ ፊቱን መምታት እና መደብደብ ሐራም ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 49 ሐዲስ 41 ቁጥር 2559
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ከእናንተ አንዱ በሚጋደልበት ጊዜ ፊትን ከመምታት ይቆጠብ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِذَا قَاتَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَجْتَنِبِ الْوَجْهَ ".
ይህ በሆነበት አግባብ ቡጢን ከዲን ጋር አያይዞ ጮቤ መርገጥ ምን ያህል ወጥ የረገረ ነገር መሆኑ ከወዲሁ የታወቀ ነው፥ ፊትን መቶ እና ደብድቦ በሚያስሸልም የሐራም ውድድር ላይ አምላካችን አሏህ ጣልቃ አይገባም። ምንም ነገር የሚከናወነው እና የሚሆነው አሏህ ፈቅዶ ቢሆንም በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ይገባል ማለት አይደለም፥ በአሏህ ፈቃድ ዙሪያ ከዚህ ቀደም የጦመርኩትን መጣጥፍ መመልከት ይቻላል፦ https://t.me/Wahidcom/4231
ብጥር እና ንጥር አድርገን ስንመለከተው ቡጢ የግሪክ ወሮም ዐረማዊ ልማድ እና የምዕራባውያን እሴት እና እሳቦት እንዲህ እርዮት አና አብዮት ነው፥ የዐረማዊ ልማድ የሚሰነፍግ እና የሚያጥነገንግ መሆኑ እየታወቀ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ዲንን ቁማር አርጎ ማስያዝ ደግሞ እጅግ ሲበዛ ክፉኛ ነገር ነው፦
22፥11 ከሰዎች በጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን የሚያመልክ ሰው አለ። ታዲያ መልካም ነገር ቢያገኘው በእርሱ ይረጋል፥ መከራ ብታገኘው በፊቱ ላይ ይገለበጣል፡፡ የቅርቢቱን ዓለም እና የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ፡፡ ይህ እርሱ ግልጽ ኪሳራ ነው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ ۖ فَإِنْ أَصَابَهُ خَيْرٌ اطْمَأَنَّ بِهِ ۖ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ انقَلَبَ عَلَىٰ وَجْهِهِ خَسِرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةَ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ
ሊክድ ወይም ሊያምን ጫፍ ላይ ሆኖ አሏህን እያመለከ ሲሳካለት ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ሳይሳካለት ከዲን የሚገለበጥ የቅርቢቱን ዓለም እና የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ፥ ስለዚህ ሐራም የሆነውን ቡጢ ይቅርና ማንኛውን ነገር በፉክክር እና በውድድር የሚደረግ ነፍሥያህ ጉዳይ ውስጥ የአሏህ እጅን አስገብቶ ቁማር መጫወት ግልጽ ኪሳራ ነው። የዓለማቱን ጌታን አሏህን ሁለት ሰዎች በሚያደርጉት ነፍሢያህ"Egocentric" ውድድር እና ፉክክር ውስጥ የአሏህን አሕካም ማስገባት ቂልነት እና ዕብደት ነው፥ ከዘር፣ ከዘውግ፣ ከቀለም፣ ከቋንቋ፣ ከብሔር፣ ከባህል ፉክክር እና ውድድር ወጥተን ሊላሂ በሚደረግ ድርጊት"Theocentric" የዓለማቱን ጌታን አሏህ ያግዘናል እጁም አለበት።
"ዐውራህ" عَوْرَة ማለት "ሐፍረተ ገላ" ማለት ሲሆን ዐውራህ የሚገለጠው በቤት ውስጥ ከፈጅር በፊት፣ በዝሁር እና ከዒሻእ በኋላ ሦስት ጊዜያት ነው፦
24፥58 ለእናንተ የኾኑ ሦስት የሐፍረተ ገላ መገለጫ ጊዜያቶች ናቸውና፡፡ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَّكُمْ ۚ لَيْسَ عَلَيْكُمْ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ሐፍረተ ገላ" ለሚለው የገባው ቃል "ዐውራት" عَوْرَات ሲሆን "ዐውራህ" عَوْرَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ ይህም ለባለ ትዳሮች ብቻ ሲሆን ነገር ግን አደባባይ ላይ ሐፍረተ ገላን ከፍቶ ለዛውም ለዓለም ሕዝብ ማሳየት ምን ያህል ሐራም መሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። ስለዚህ ቡጢ ሰውን የሚጎዳ፣ ቁማር እና ሐፍረተ ገላ የሚታይበት ስለሆነ ሐራም ነው።
እንደ ጥቅል ለመረዳት በፉክክር እና በውድድር ውስጥ የአሏህ ቀደማይ ፈቃድ"Antecedent Will" የሌለበት ቢሆንም ማንኛውምን ግጥሚያ የሚያሸንፈው ጠንክሮ የተለማመደ፣ ስልት ያለው እና የተሻለ ዝግጅት ያደረገው ሰው መሆኑ የአሏህን ደኃራይ ፈቃድ"Consequent Will" ነው። በቡጢ ሰውን የሚጎዱትን አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! እኛንም ሰውን ከመጉዳት ይጠብቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
August 28, 2026 8.4K 11 61