ድንግል ማርያም
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥47 "ጌታዬ ሆይ! "ወንድ ያልነካኝ" ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል" አለች፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ
በዕብራይስጥ "በቱላህ" בְּתוּלָה ማለት "ድንግል" ማለት ነው፥ በታናኽ "በቱላህ" בְּתוּלָה በነጠላ 32 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ወንድ የማያውቃት ድንግል ሴት ናት፦
ዘፍጥረት 24፥16 ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት "ድንግል" ነበረች። וְהַנַּעֲרָ֗ טֹבַ֤ת מַרְאֶה֙ מְאֹ֔ד בְּתוּלָ֕ה וְאִ֖ישׁ לֹ֣א יְדָעָ֑הּ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ድንግል" ለሚለው የገባው ቃል "በቱላህ" בְּתוּלָה ነው፥ ይህቺ ሴት ርብቃ ስትሆን እርሷ ድንግል ብቻ ሳትሆን ቆንጆ ወጣት ሴት ነበረች፦
ዘፍጥረት 24፥43 ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም "ቆንጆ" ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ። וְהָיָ֤ה הָֽעַלְמָה֙ הַיֹּצֵ֣את לִשְׁאֹ֔ב וְאָמַרְתִּ֣י אֵלֶ֔יהָ הַשְׁקִֽינִי־נָ֥א מְעַט־מַ֖יִם מִכַּדֵּֽךְ׃
እዚህ አንቀጽ ላይ "ቆንጆ" ለሚለው የገባው ቃል "አልማህ" עַלְמָה ሲሆን "ኮረዳ" "ወጣት ሴት" "ብላቴናይት" ማለት ነው፦
ዘጸአት 2፥8 "ብላቴናይቱ" ሄዳ የሕፃኑን እናት ጠራች። הָֽעַלְמָ֔ה וַתִּקְרָ֖א אֶת־אֵ֥ם הַיָּֽלֶד׃
ምሳሌ 30፥19 የሰው መንገድ ከ-"ቆንጆ" ጋር ነው። וְדֶרֶךְ גֶּבֶר בְּעַלְמָה
በታናኽ "አልማህ" עַלְמָה የሚለው ቃል 7 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን "ብላቴናይት" "ቆንጆ" "ኮረዳ" "ወጣት ሴት" ማለት ነው፥ "ኤሌም" עֶלֶם ማለት "ብላቴና" "ቆንጆ" "ጎረምሳ" "ወጣት ወንድ" ማለት ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥56 ንጉሡም፦ "ይህ "ብላቴና" የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይቅ" አለ። נו וַיֹּאמֶר, הַמֶּלֶךְ: שְׁאַל אַתָּה, בֶּן-מִי-זֶה הָעָלֶם.
1ኛ ሳሙኤል 20፥22 "ብላቴናውን" ግን፦ "እነሆ ፍላጻው ከአንተ ወዲያ ነው" ያልሁት እንደ ሆነ ያህዌህ አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ። כב וְאִם-כֹּה אֹמַר לָעֶלֶם, הִנֵּה הַחִצִּים מִמְּךָ וָהָלְאָה--לֵךְ, כִּי שִׁלַּחֲךָ יְהוָה.
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ብላቴና" ወይም "ወጣት ወንድ" ለሚለው የገባው ተዕባታይ ቃል "ኤሌም" עֶלֶם ነው፥ ስለዚህ "ኤሌም" עֶלֶם የሚለው ተባዕታይ መደብ ሆነ "አልማህ" עַלְמָה የሚለው አንስታይ መደብ "ድንግል" ማለት በፍጹም አይደለም። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች የሚራኮቱበትን ጥቅስ በቅጡ እና በአግባብ መመልከት ይቻላል፦
ኢሳይያስ 7፥14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ "ወጣት ሴት" ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች።לָכֵן יִתֵּן אֲדֹנָי הוּא, לָכֶם–אוֹת: הִנֵּה הָעַלְמָה, הָרָה וְיֹלֶדֶת בֵּן, וְקָרָאת שְׁמוֹ, עִמָּנוּ אֵל.
የክርስቲያን መተርጉማን፦ 1. NET Bible 2. New American Bible 3. Good News Translation 4. New Revised Standard Version "ወጣት ልጅ"a young woman" ብለው በትክክሉ ተርጉመውታል። በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን እና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ሲሉ አካዝ የተሰጠው ምልክት ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ መሆን ነው፦
ኢሳይያስ 7፥16 ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ የፈራሃቸው "የሁለቱ ነገሥታት" አገር ባድማ ትሆናለች።
ቢኢሳይያስ ዘመን የነበረችው ያቺ ወጣት ሴት ነቢይቱን ሕፃኑን ወለደችው፥ ኢሳይያስም ያ ከወጣቲቱ ሴት የተወለደውን ሕፃን በወቅቱ በሁለተኛ መደብ "አማኑኤል ሆይ" እያለ ያናግረው ነበር፦
ኢሳይያስ 8፥3 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች።
ኢሳይያስ 8፥8 አማኑኤል ሆይ! የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።
ይህ አማኑኤል የተባለው ሕፃን አባት እና እናት ያለው ሕፃን ሲሆን ሕፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብት እና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት በመወሰድ ትንቢቱ ተፈጽሟል፦
ኢሳይያስ 8፥4 "ሕፃኑ "አባቱን" እና እናቱን መጥራት ሳያውቅ የደማስቆን ሀብት እና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና" አለኝ።