ይህ የቀደምት ሠለፎች ዐቂዳህ ሆኖ ሳለ የራሳቸው ሥነ መለኮት የማያውቁ የክርስትና ዘለሰኛ ሚሽነሪዎች አምላክ… — ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics" — TG.ME

ይህ የቀደምት ሠለፎች ዐቂዳህ ሆኖ ሳለ የራሳቸው ሥነ መለኮት የማያውቁ የክርስትና ዘለሰኛ ሚሽነሪዎች አምላክ "ፊት" እንዳለው እና አማንያን በፍርድ ቀን ፊቱን እንደሚያዩ በቅጡ አልተረዱም፦
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ “ሰው አይቶኝ አይድንምና "ፊቴን" ማየት አይቻልህም፡” አለ። וַיֹּאמֶר, לֹא תוּכַל לִרְאֹת אֶת-פָּנָי: כִּי לֹא-יִרְאַנִי הָאָדָם, וָחָי.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓኒም" פָנִים ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት ደግሞ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ነው፦
ዘጸአት 33፥20 ደግሞም፦ “ሰው አይቶኝ አይድንምና "ፊቴን" ማየት አይቻልህም፡” አለ። καὶ εἶπεν· οὐ δυνήσῃ ἰδεῖν τὸ πρόσωπόν μου· οὐ γὰρ μὴ ἴδῃ ἄνθρωπος τὸ πρόσωπόν μου καὶ ζήσεται.

አምላክ "ፊቴ" እያለ "ፊት የለህም" ብሎ ከእርሱ ጋር ሙግት መግጠም ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? የአምላክ ፊት ማንም በዚህ ዓለም ማየት አይችልም። አምላክ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ሰለሚኖር እርሱን መቼም ቢሆን ከቶ አንድ ስንኳ ያየ የለም፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥12 አምላክን ማንም ከቶ አላየውም። Θεὸν οὐδεὶς πώποτε τεθέαται·
ዮሐንስ 1፥18 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው አንድ ስንኳ የለም። Θεὸν οὐδεὶς ἑώρακεν πώποτε·
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም። ὃν εἶδεν οὐδεὶς ἀνθρώπων οὐδὲ ἰδεῖν δύναται·

የጥንት ሰዎች የአምላክ ፊት ለማየት ይጓጓሉ፦
መዝሙር 42፥3 ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች። መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ "ፊት" መቼ አያለሁ? צָמְאָ֬ה נַפְשִׁ֨י ׀ לֵאלֹהִים֮ לְאֵ֢ל חָ֥֫י מָתַ֥י אָב֑וֹא וְ֝אֵרָאֶ֗ה פְּנֵ֣י אֱלֹהִֽים׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፓኒም" פָנִים ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት ደግሞ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ነው፥ አምላክን በትንሣኤ አካል ማየት የነቢያቱ እሾት ነው፦
ኢዮብ 19፥26 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ አምላክን እንዳይ አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼም ይመለከቱታል።
ራእይ 22፥3 ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ። καὶ οἱ δοῦλοι αὐτοῦ λατρεύσουσιν αὐτῷ, καὶ ὄψονται τὸ πρόσωπον αὐτοῦ,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ሲሆን በፍርድ ቀን ትልቁ የቅድስና ደረጃ እና ማዕረግ ነጽሮተ አምላክ ነው፦
ማቴዎስ 5፥8 ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ አምላክን ያዩታልና።
ዕብራውያን 12፥14 ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።

አላጋጮሻቹ እነዚህን አናቅጽ ሲመለከቱ ምን ይውጣቸው ይሆን? "መንጦላዕት" ማለት "መጋረጃ" ማለት ነው፥ "ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ" ማለት አማኞች በቅድስና ከፍ ወዳለ ደረጃ ሲደርሱ በመንጦላዕት ያሉትን ሦስት ፊቶች በንጽሕ ልብ እና በዓይነ ሥጋ የማየት ከፍተኛው ደረጃ እና ማዕረግ ነው። የሚገርመው በእኛ ዐቂዳህ የትንሣኤ ቀን የሚታየው አምላክ አንድ ማንነት ሲሆን በእነርሱ ግን የሥላሴ ሦስት ፊቶች ናቸው፥ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ስለ ሦስቱ ፊቶች እንዲህ ይናገራል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 29
"የሥሉስ ቅዱስ የሚሆኑ ሦስት አካላት፣ "ሦስት ገጻት" እና ሦስት መልክአት እንዳሉት ስለ መለኮት የተነገረውን ሁሉ እናምናለን"።

"ሦስት ገጻት" የሚለው ይሰመርበት! በግዕዝ "ገጽ" ማለት "ፊት" ማለት ሲሆን "ገጻት" ማለት "ፊቶች" ማለት ነው፥ ከአንድ በላይ የሆኑ ሦስት ፊቶችን "እንመለከታለን" የሚል ተስፋችሁ አንቀጸ እምነታችሁ ከሆነ እንግዲያውስ ሙሥሊሞች በትንሣኤ ቀን በትንሣኤ አካል የአሏህን ፊት በጀናህ መመልከታችን ሊያስደንቃችሁ አይገባም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
August 24, 2026 11.8K 3 29