የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም!
ሁለንተናዊ ከፍታ ያለው በመኖራቸው ላይ አያበቃም ወደ አኼራ መሻገራቸውም ስኬታማነታቸውም እንዲያበቃ አያደርግም።
"መኖሬም ለእናንተ ኸይር ነው ሞቴም እንደዛው" ሰው በህይወት ውስጥ እያለ ስለ ራሱ ከኖር እና በራሱ የህይወት መስመር ውስጥ ካለፈ የግል ስኬቱ ሊሆን ይችላል ቀሪ ማንነት ግን ብዙ አይኖረውም። ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለፉትን 1440 አካባቢ አመታት ያለምንም ሶሻል ሚዲያና ቀሪ ምስል እና ቪዲዬ እና ፎቶ በተደራጀ መልኩ ማንነታቸውን ሚያጠና ግሩፕ ንግግራቸው ላይ እንዳይዋሽ።
ሰሂህ ፣ ደኢፍ ፣ ሀዲሱ ገሪብ እየተባለ እዚህ ድረስ አወራራቸው አረማመዳቸው ሳይቀር ተገልፇል። በብዙዎች ሲጠቀስ ያለው ባህሪያቸው ፣ ስብእናቸው ፣ ቸርነታቸው ፣ ዱንያን አቅለው መኖራቸው ነው።
በዚህ ልክ ምራቁ መሬት ማይነካ ማንነት ያለው ታላቅ ሰው ሚበላው አጥቶ እንደነበረ ማሰብ እና በረሃብ ድንጋይ አስሮ እንደነበረ ማሰብ ምን ያህል የሰው ልጅ ከሳቸው ማንነት ብዙ መማር እንዳለበት ያሳያል ከዱንያ ሰውነት የአኼራ ሰው መሆን የተሻለ ነው።
ቢሹ ከሰማይ ወርቅ ማዘነብ እየቻሉ ፣ ሲያሻቸው ደሞ የተመረጡ ምግቦችን መብላት እየቻሉ እንዴት ለምን ዝም አሉ የዘወትር ጥያቄዬ ነው።
ሆኖም ግን መልካም ስትሆን ፣ ስምህ ከቀብር በላይ ዳግም ይነሳል ስለዚህም ስትሞት በዙሪያህ ያሉ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ሰው ማያቃቸው ሰዎች አባታቸው እንደሞተ እንዲሰማቸው አድርገህ በአንተ መሞት ሚጐዱ ሰዎች መኖር አለባቸው። መኖርህም ጥቅም አልባ እንዳይሆን መሞትህም ከቁጥር ማጉደል በዘለል ትርጉም ማይኖረው አታድርግ።
ረሱል መኖራቸው ብዙ ትርጉም ነበረው አሁንም ቢሆን ስማቸው ለችግሮች ሁሉ መክፈቻ ቁልፍ ነው።
5
1December 14, 2024 1.3K 3