ፈርድ (ግዴታ የኾኑ ተግባራት) ላይ በመወጠር ከነፍል (ትርፍ ወይም ተጨማሪ) ተግባራትን መዘናጋት ዑዝር (ምክንያት) የሚሰጥለት ነገር ሊኾን ይችላል። በተቃራኒው ትርፍ በሚባሉ (ነዋፊል) ተግባራት በመወጠር ከፈርድ (ግዴታ ተግባራት) መዘናጋት ግን ከትርፉ ጉዳቱ ሊበልጥ ይችላል።
#የረቢዕ ወር ፈርዱ በቅድሚያ ራስን ወደ ነብያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐድራ ማቃረብና ከእርሳቸው ጋር ያልንን አደብ መፈተሽ ነው። ሲራቸውን መማማር በጥሩ ነሻጣ ላይ መኾንን መበረታታት ነው።
#መውሊድ ፈርዶች የሚገነቡበት የዑለማዎች ሱና እንጂ ለነፍል ባልደረሰ ተግባር የምንባክንነት አይደለም። መውሊድ ዑለማዎች ማሕበረሰብን በመሐባ ወደ እምነት ያስገቡበት ተርቲባቸው ነው። የሐቂቃ መሐባ ከእምነት ነው። መሐባ የሌለው ተግባር ድካም ነው።
ፈርድ በኾኑ ተግባራት ላይ የምንጸናበት፣ ሱናቸውን የምናጠናክርበት፣ ከአላስፈላጊ ምግባራት የምንቆጠብበት የረቢዕ ጊዜ ያድርግልን።













